በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ 69 ሚሳዬሎችን ዩክሬን ላይ አስወነጨፈች


በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት ሩሲያ ባካሄደችው የቦምብ ድብደባ በተጎዳ የመኖሪያ ህንፃ ፊት ለፊት አንዲት ሴት ወደ ሰብዓዊ ርዳታ ማከፋፈያ ቦታ ስታመራ - ታህሳስ 28፣ 2022
በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት ሩሲያ ባካሄደችው የቦምብ ድብደባ በተጎዳ የመኖሪያ ህንፃ ፊት ለፊት አንዲት ሴት ወደ ሰብዓዊ ርዳታ ማከፋፈያ ቦታ ስታመራ - ታህሳስ 28፣ 2022

አዲስ ዓመት ሊገባ ሁለት ቀን ሲቀረው ሩሲያ ወደ ዩክሬን መዲና ኪቭ እና ሌሎች ከተሞች በደርዘን በሚቆጠሩ ሚሳዬሎችን ዛሬ ማስወንጨፏን የዩክሬን ባልስልጣናት አስታውቀዋል።

የዩክሬን ሚዲያ ሴንተር እንዳስታወቀው ከተወነጨፉት 69 ሚሳዬሎች ውስጥ 54 የሚሆኑትን ዩክሬን ተኩሳ ጥላለች።

በኪቭና በመላው ዩክሬን የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ለአምስት ሰዓታት ያህል ሲጪህ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የተሰጠ ረጅሙ ማስጠንቀቂያ መሆኑም ታውቋል።

የዩክሬኑ ብርጋዴር ጄኔራል ኦሌክሲ ሮሞቭ እንዳሉት ሩሲያ ያነጣጠረችው በዩክሬን ወሳኝ በሆኑና የሃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ነበር።

ከሚሳዬሎቹ ጥቃት ቀደም ብሉ ‘ካማካዚ’ በተሰኙ ድሮኖች በምሽት ጥቃት መፈጸሙም ታውቋል።

ሩሲያ በርካታ የአይር ጥቃቶችን በዩክሬን ላይ በመፈጸም ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን በማውደሟ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እጅግ ቀዝቃዛማ የሆውን የክረምት ወቅት ያለ ኤሌክትሪክና ሙቀት ለመጋፈጥ ተገደዋል።

የዛሬው የሚሳዬል ጥቃት የተደረገው ሩሲያ ዩክሬን ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ ወደጎን በመተው፣ በዩክሬን የሚገኙ አራት ግዛቶች ወደ ሩሲያ የመጠቅለላቸውን ጉዳይ ኪቭ

XS
SM
MD
LG