በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሞምባሳ-ናይሮቢ የተዘረጋው የባቡር መሥመር ለአዲስ ዓመት ጉዞ ተዘጋጅቷል


የኬንያ የባቡር መንገድ አስተናጋጆች ስራ የጀመረውን ባቡር ለመቀበል በዝግጅት ላይ ናቸው።
የኬንያ የባቡር መንገድ አስተናጋጆች ስራ የጀመረውን ባቡር ለመቀበል በዝግጅት ላይ ናቸው።

ከሞምባሳ ናይሮቢ በቻይና የተዘረጋው የባቡር መስመር ለአምስት ዓመታት ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠቱ ብቻ ሳይሆን፣ የነዋሪዎችን የጉዞ ልምድ የቀየረ ነው ሲል የቻይና ማዕከላዊ ቴሌቪዥን (ሲ.ሲ.ቲቪ) ዘገባ አመልክቷል።

480 ኪ.ሜ. ርቀት ያለው የባቡር መንገድ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ወደብ የሆነውን ሞምባሳን ከናይሮቢ ጋር ያገናኛል። ለነዋሪው አማራጭ መጓጓዣም ሆኗል፡

ኬንያውያን አዲሱን ዓመት ለመቀበል በሚዘጋጁበት በዚህ ወቅት፣ የባቡር ተጠቃሚዎች ቁጥር በመጨመር ላይ ነው።

ስታንዳርድ ጌጅ ሬይልዌይ (ኤስ.ጂ.አር) ብለው የሚጠሩት የባቡር መሥመር 10 ሺህ ተጓዦችን በቀን የሚያስተናግድ ሲሆን በሚጠናቀቀው የፈረንጆቹ የመጨረሻ ወር ዲሴምበር የባቡር መሥመሩ 270ሺህ ጉዞዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም 11.8 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው ተብሏል።

በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ደግሞ በአጠቃላይ ከ2.39 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቅ ሲሆን የ19.3 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተግሯል።

በአዲስ ዓመት አከባበር ምክንያት ሊጨምር ለሚችለው የተጓዦች ቁጥር መዘጋጀታቸውን የባቡር ኮባንያው ሠራተኞች ይናገራሉ።

በቻይና መዋዕለ-ንዋይ የተገነባው የባቡር መሥመር ኬንያ በእ.አ.አ 1963 ነጻነቷን ካወጀች ወዲህ ትልቁ ፕሮጀክት ነው ተብሏል።

XS
SM
MD
LG