በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳስ ከእስር ተፈቱ


ኣቡነ ፍቕረማርያም ሓጎስ
ኣቡነ ፍቕረማርያም ሓጎስ

የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰገነይቲ አገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ፍቅረ ማሪያም ሐጎስ ዛሬ ረቡዕ ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።

ባለፈው ጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ከውጭ አገር እንደተመለሱ በሃገሪቱ ባለስልጣናት 'ይፈለጋሉ' ተብለው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው የቆዩት አቡነ ፍቅረማርያም ሐጎስ መፈታታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀዋል።

እርሳቸው በታሰሩበት ዕለት መታሰራቸው የሚገለጸው የሰገነይቲ ቆሞስ አባ ምሕረተ አብ እስጢፋኖስም ዛሬ መፈታታቸው ተገልጿል።

አቡነ ፍቅረ ማርያም የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ካሏት አራት ሰበካዎች አንዱ የሆነው የሰገነይቲው ሰበካ መሪ እንደነበሩ ይታወቃል።

ስለአቡነ ፍቅረ ማርያም መታሰርም ሆነ መፈታት እስካሁን ከኤርትራ ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም።

XS
SM
MD
LG