በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ እናትና ልጅ መቀሌ ላይ ተገናኙ


ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ እናትና ልጅ መቀሌ ላይ ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:51 0:00

ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ እናትና ልጅ መቀሌ ላይ ተገናኙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ ዓመት ከሰባት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መንገደኞቹን አሳፍሮ መቀሌ ገብቷል። ተሳፋሪ መንገደኞቹም ከረጅም ግዜ በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በመገናኘታቸው ደስታቸውን የገለፁ ሲሆን ሌሎች ቤተሰቦችም መገናኘት እንዲችሉ ሁሉም መስመሮች እንዲከፈቱ ጠይቀዋል።

"በጣም በጣም ከመጠን በላይ ደስ ብሎኛል። ልጄን ግርማይን አገኘሁ። ሕይወቴን አገኘሁ። የወንድሞቼን ምትክ አገኘሁ። ዛሬ ነጋልኝ።" ያሉን ወይዘሮ አበራሽ ኃይለ የተባሉ እናት "የቀሩት ልጆቻችችን እንዲመጡ፣ ሰላም እንዲሆንልን፣ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ በደስታ ወደ ቤቱ እንዲገባ፣ፀሐያችን እንዲወጣልን፣ እንደቀደመው እንዲሆንልንና፣አብረን እንድንበላ እንድንጠጣና ተመስገን እንድንል ነው የምፈልገው።" ብለዋል።

በሌላ በኩል "የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያንን በማገናኘቱ ደስተኛ ነው" ሲሉ የኩባንያው ዋና ሥራ አሰፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

አየር መንገዱ ከሁለት ዓመታት በኋላ ዛሬ ወደ መቀሌ የጀመረውን በረራ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የዛሬው ደርሶ መልስ በረራ የተሳካ እንደነበርም ገልጸዋል።

ዛሬ በአንድ አውሮፕላን የተጀመረው የመቀሌ በረራ ከነገ ጀምሮ ደግሞ በቀን ወደ ሁለት ከፍ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ሽሬ መብረር እንደሚጀምርም አስታውቀዋል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG