በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናታንያሁ መንግስት የዌስት ባንክ ሰፈራ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስታወቀ


ፋይል - የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሊኩድ ፓርቲ መሪ ቤንጃሚን ናታንያሁ የመጀመሪያው የእስራኤል ፓርላማ ምርጫ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኃላ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ - ህዳር 2, 2022.
ፋይል - የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሊኩድ ፓርቲ መሪ ቤንጃሚን ናታንያሁ የመጀመሪያው የእስራኤል ፓርላማ ምርጫ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኃላ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ - ህዳር 2, 2022.

አዲስ የተመሰረተው የቤንጃሚን ናታንያሁ መንግስት የዌስት ባንክን ሰፈራ ማስፋፋት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዝርዝሮች ቀዳሚው መሆኑን አስታወቀ። ከጥምር መንግስቱ ጋር በገቡት ስምምነት መሰረትም፣ በደርዘን የሚቆጠሩ በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ከከተማ ወጣ ያሉ መኖሪያዎችን ህጋዊ እንደሚያደርግ እና ተይዘው የነበሩ አካባቢዎችን እንደሚቆጣጠርም ቃል ገብቷል።

አዲሱ መንግስት ቃለመሃላ ከሚፈፅምበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ይፋ የተደረገው የጥምር መንግስቱ ስምምነት ሀይማኖታዊ ምክንያትን በማስቀመጥ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ላይ ለሚደርስ መድሎ ድጋፍ እና ከስራ ይልቅ ትምህርትን ለሚመርጡ አክራሪ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወንዶች ጠቀም ያለ የገንዘብ ድጎማ እንደሚሰጥ አስታውቋል።


አጠቃላይ ስምምነቱ የናታንያሁ መንግስት ስራውን ሲጀምር ለሚጠብቀው ውሽንፍር የበዛበት ስራ መሰረት የጣለ እና ከአብዛኛው የእስራኤል ህዝብ እና በውጭ ያሉ የቅርብ አጋሮች ጋር ግጭት ውስጥ ሊከተው የሚችል መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዝርዝር የተቀመጡት መመሪያዎች፣ በመፅሃፍ ቅዱስ 'ጁዲያ እና ሳማሪያ' በመባል የተጠቀሱትን የዌስት ባንክ ግዛቶችን ጨምሮ "በእስራኤል ምድር በሙሉ ሰፈራዎችን ማስፋፋት እና ማሳደግ" በሚል ቁርጠኝነት የተመራ ነው።


እስራኤል የጋዛ ሰርጥን እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ጨምሮ ዌስት ባንክን የተቆጣጠረችው እ.አ.አ በ1967 ዓ.ም ሲሆን ፍልስጤማውያን ዌስትባንክን ወደፊት የሚኖራቸው ነፃ ሀገር እምብርት አድርገው ይቆጥሩታል። እስራኤል በቦታው ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይሁድ ሰፈሮችን ገንብታ በአሁኑ ወቅት ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ እስራኤላውያንን ከ2.5 ሚሊየን ፍልስጤማውያን ጋር ይኖሩበታል።

XS
SM
MD
LG