በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የወጭ ህግ የኢራን ዜጎችን ወከባና ክትትል ማዕቀብ አካቷል


ፋይል - ኢራንያዊ ተቃዋሚ ማሲህ አሊነጃድ ከአሶስዬትድ ፕሬስ ጋር ቃለምልልስ ስታካሂድ በኢራን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ የተገደለች አንዲት ሴት ፎቶ ይዛ - መስከረም 23, 2022
ፋይል - ኢራንያዊ ተቃዋሚ ማሲህ አሊነጃድ ከአሶስዬትድ ፕሬስ ጋር ቃለምልልስ ስታካሂድ በኢራን እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ የተገደለች አንዲት ሴት ፎቶ ይዛ - መስከረም 23, 2022

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ዜጎችን በማወከብና በመከታተል ለኢራን መንግሥት የሚሰሩትን ሰዎች ተጠያቂ የሚያደርገውን “የማሺ አሊነጃድ ወከባና ህገወጥ ዒላማ ህግ” ማስፈጸሚያን ጨምሮ ባላፈው ሳምንት የ1.7 ትሪሊዮን ዶላር የወጭ ረቂቅ አሳልፏል፡፡

“የማሺ አሊነጃድ ወከባና ህገወጥ ዒላማ ህግ” የተሰየመው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ፐርሽያ (ፋርስ) ቴሌቭዥን አዘጋጅና የኢራንን መንግሥት በመተቸት በምትታወቀው እንዲሁም ወደ ኢራን ታፍና እንድትመለስ ሴራ በተፈጸመባት ጋዜጠኛ ስም ነው፡፡

የወጣው ህግ ላይ ”የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ ኢራን ውስጥ፣ ለሰብአዊ መብቶችና ነጻነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቆሙትን ግለሰቦች ይከታተላል፣ ያዋክባል፣ ያሸብራል፣ ያሰቀያል፣ ያፍናል፣ ይገድላል፣ ንጽኋን ተቋማትና ግለሰቦች በኢራን መንግሥት የአገዛዙ ጠላት ተደርገው ተፈርጀዋል፣ በዩናይድ ስቴትስ ምድር የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ጨምሮ የውጭ ዜጎችን አፍኖ ይወስዳል” የሚል ክሶች ሰፍረዋል፡፡

ውሳኔው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢራን የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታን ጨምሮ፣ የኢራን መንግሥት ባላፈው ዓመት ውስጥ በኢራን ውስጥና ከኢራን ውጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች ዒላማ በማድረግ የወሰዳቸው እምርጃዎችና፣ ተቺዎቹን ዝም ለማሰኘት የገንዘብ ድጋፍ ስለሚያደርግበት መንገድ ዝርዝር መረጃዎች ሪፖርት እንዲያቀርብ ያዛል፡፡

በየዓመቱ የሚታደሰው ሪፖርት ሰዎችን በማወከብ፣ በመከታተል፣ አፍኖ በመወሰድ፣ በማሰቃየትና በመግደል ለሚንቀሳቀሰው ለኢራን መንግሥት የሚሰሩትን እንዲሁም የኢራንን መንግሥት ህገ ወጥና ሙስናዎች ማጋለጥ የሚፈልጉትን የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ሁኔታ ለይቶ እንዲያመለክት የሚያዝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከኢራን መንግሥት ጋር በማበር በተጠቀሱ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚጣለው ማዕቀብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ፣ የተፈቀደላቸው ቪዛቸው እንዲሰረዝና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚያዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር ሆን ብለው እያወቁ የገንዘብ ልውውጥ የሚያካሂዱ የውጭ ፋይናንስ ተቋማትም ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል ህጉ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG