በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትሱ ቅዝቃዜ ከ3ሺ800 በላይ በረራዎች ተሰረዙ


'ቦምብ አውሎ ነፋስ' በመባል የሚጠራው የአየር ሁኔታ ክስተት በረራዎችን አስተጓጉሏል
'ቦምብ አውሎ ነፋስ' በመባል የሚጠራው የአየር ሁኔታ ክስተት በረራዎችን አስተጓጉሏል

ሰሞኑን መላውን ዩናይትድ ስቴትስ ነፋስና በረዶ ቀላቅሎ በመታው ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ ትናንት ሰኞ ብቻ ከ3ሺ 800 በላይ አየር መንገድ በረራዎች መቋረጣቸው ተነገረ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 2ሺ800 ወይም 70 ከመቶ የሆኑት በአገሪቱ ደቡብና ምዕራብ የሚሰማራው የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ በረራዎች መሆናቸውን የበረራዎችን ሁኔታ የሚከታተለው ፍላይትአዌር አስታውቋል፡፡

የመነሻና መድረሻ በረራቸው እንዲዘገይ ከተደረጉት 7ሺ100 በረራዎች መካከል በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

የበረራዎች መስተጓጎል ሰሞኑን ከተከበረው የአውሮፓውያን የገና በዓል ዋዜማ አንስቶ ዛሬ ድረስ የዘለቀ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

አብዛኛውን ዩናይትድ ስቴትስን የመታው ቀዝቃዛው የአየር ጠባይ እስከዛሬ ማክሰኞ ድረስ የሚቀጥል መሆኑ የተነገረ ሲሆን በትንሹ የ48 ሰዎችን ህይወት መንጠቁ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG