በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ጥያቄዬን ልትመልስ ትችላለች ካልሆነ ሠራዊቱ ይመልሰዋል - ሩሲያ


በገና እለት የደረሰውን የቦምብ ጥቃት ጨምሮ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርሰው ጥቃት በቀጠለበት ወቅት፣ የ61 አመቱ ቮሎድሚር እና የ51 አመቷ ናታሊያ በሚሳይል ጥቃት የደረሰበትን የፋብሪካ ህንፃ አልፈው ይጓዛሉ -ታህሳስ 25, 2022
በገና እለት የደረሰውን የቦምብ ጥቃት ጨምሮ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርሰው ጥቃት በቀጠለበት ወቅት፣ የ61 አመቱ ቮሎድሚር እና የ51 አመቷ ናታሊያ በሚሳይል ጥቃት የደረሰበትን የፋብሪካ ህንፃ አልፈው ይጓዛሉ -ታህሳስ 25, 2022

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት የሚወሰኑት ዩክሬናውያን ናቸው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ሩሲያ ጦርነቱን ከ10 ወራት በፊት ባካሄደችው ወረራ የጀመረችው ቢሆንም ላቭሮቭ “ዩክሬን ትርጉም አልባ ተቃውሞዋን በማናቸውም ሰዓት ማቆም ትችላለች” ማለታቸውን የሩሲያ ዜና አገልግሎት ታስ ዘግቧል፡፡ ላቭሮቭ “ዩክሬን የሩሲያን ጥያቄ የማታሟላ ከሆነ ጉዳዩ በሩሲያ ጦር እልባት ይሰጠዋል” ብለዋል፡፡

የሩሲያ ጥያቄ አካባቢውን ከጦር ኃይልና ከናዚ ተጽእኖ ነጻ ማድረግ መሆኑን ዩክሬን ታውቃለች ያሉት ላቭሮቭ ሩሲያ በኃይል የጠቀለለቻቸውን አራት ግዛቶችን ጨምሮ ከዩክሬን ግዛት ለሩሲያ ስጋት የሆነውን ማስወገድ የሩሲያ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ሩሲያ ወታደሮችዋን ከዩክሬን ግዛቶች ለቀው እንዲወጡ በማድረግና የዩክሬን የግዛት አንድነትና ነጻነት በማክበር የጀመረችውን ጦርነት በፈለገችው ጊዜ ማቆም ትችላለች ብለዋል፡፡

“ሩሲያ ያላትን ኃይሏን ሁሉ አሟጣ እየተጠቀመች ነው” ሲሉ የተናገሩት ዘሌነስኪ ሩሲያ ባደረሰችው ውድመት ዩክሬን ውስጥ 9 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ያለምንም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሮ ኩሌባ ትናንት ሰኞ ቀደም ብለው ከአሶሴትይት ፕሬስ ጋር በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ መሪነት የሚካሂደው የሰላም ጉባኤ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ በጉባኤው ላይ ትካፈላለች ብለው እንደማይገምቱም ሚኒስቴሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG