በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒጀር የዶር እርባታ ከፍተኛ የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ ተከሰተ


ፋይል -የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ
ፋይል -የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ

በኒጀር በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ የሆነው የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ ወረረሽኝ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል በሚገኝ አንድ የዶር እርባታ ውስጥ መከሰቱን የዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል፡፡

ታሆኣ በተባለ ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተው ወረረሽኝ 4920 የሚሆኑትን ሲገድል የተቀሩትም መታረዳቸውን የኒጀር ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ወረርሽኙ እ.አ.አ ከሀምሌ 2021 ወዲህ በኒጀር ሲከሰት የመጀመሪያው መሆኑን አመልክቶ በሽታው የተከሰተው መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ከዚንደር ግዛት ታዘው በመጡ ዶሮዎች ላይ መሆኑን ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተወሰነው የአፍሪካ ክፍል ባልተለመደና በዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ ከ100 ሚሊዮን በላይ ወፎችን በገደለው ዓለም አቀፍ የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ መመታቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG