በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያ ድሮኖች ደቡብ ኮሪያን ግራ አጋብተዋል


ፋይል - የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ በሚካሄደው ስድስተኛው የሰራተኞች ፓርቲ ስምንተኛው ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በተገኙ ወቅት - ታህሳስ 26, 2022።
ፋይል - የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ በሚካሄደው ስድስተኛው የሰራተኞች ፓርቲ ስምንተኛው ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በተገኙ ወቅት - ታህሳስ 26, 2022።

የደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናት የአገሪቱን የአየር ክልል ጥሰው ከገቡ አምስት የሰሜን ኮሪያ የቅኝት ድሮኖች መካከል አንዳቸውን እንኳ መትተው መጣል ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ቁጭት ገልጸው ለወደፊቱ ግን ይህ የማይደገም መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ለስለላ ከላከቻቸው ድሮኖች መካከል በተለይ አንደኛው ወደ ሰሜን ኮሪያ ከመመለሱ በፊት ትናንት ሰኞ ከሰዓት በኋላ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሶል አካባቢ ሲያዣብብ ቆይቶ ከሶስት ሰዓት በኋላ ወደ ሰሜን ኮሪያ መመለሱ ተነገሯል፡፡

የአገር ውስጥ የዜና አውታሮች አንደኛው ድሮን በማዕከላዊ የአገሪቱ ዋና ከተማ በደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አካባቢ ሲበር የተመለከቱ መሆኑን ዘግበዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የመካላከያ ሚኒስቴር ግን በፕሬዚዳንቱ ጽቤት አካባቢ ምንም ነገር ያየው ነገር አለመኖሩን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ አራቱ ድርኖች አሁን ድረስ የት እንደገቡ መታወቅ አለመቻሉን የደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የጋራ ጦር አዛዥ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ የአገሪቱ የአየር መከላከያ ስጋት የደቀኑትን የሰሜን ኮሪያን የታጠቁ ድሮኖችን ወዲያውኑ ተመልክቶ መትቶ ለመጣል የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ትናንት ሰኞ የደቡብ ኮሪያን አየር ክልል ጥሰው የገቡ ድርኖች ከሶስት ሜትር ያነሰ ርዝማኔ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሰሜን ኮሪያ ጥቃቃን ሰው አልባ ድሮኖች የአየር ክልሏ የተወረረው ደቡብ ኮሪያ ለአጸፋው የአየር መከላከያዋን እንድምታጠናክር የአገሪቱ ጦር አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ክስተቱ የደቡብ ኮሪያን የመከላከል አቅም ከጥያቄ ውስጥ የከተተ አጋጣሚ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የላከቻቸው የቅኝት ድሮኖች የጦር መሳሪያ ያልተገጠመላቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG