በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የዩክሬንን ድሮን መታ መጣሏን አስታወቀች


አንድ የዩክሬን ወታደር ዶኔትሴክ ግዛት ውስጥ ከመሬት በታች ከሚገኝ የትዕዛዝ ማዕከል ሆኖ ከድሮን የሚተላለፈው መረጃ ሲከታተል። ታህሳስ 25, 2022. (AP Photo/Libkos)
አንድ የዩክሬን ወታደር ዶኔትሴክ ግዛት ውስጥ ከመሬት በታች ከሚገኝ የትዕዛዝ ማዕከል ሆኖ ከድሮን የሚተላለፈው መረጃ ሲከታተል። ታህሳስ 25, 2022. (AP Photo/Libkos)

የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬናውያንን ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ዛሬ ሰኞ መትተው መጣላቸውን የአገሪቱን መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅሶ የሩሲያ ዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ተመትቶ ወድቋል የተባለው የድሮኑ ስብርባሪም በደቡብ የአገሪቱ ክፍል በሚገኘው የጦር ሰፈር ላይ በማረፍ ሶስት ሰዎችን መግደሉን ዘገባው አመልክቷል።

ድሮኑ ሳራቶቭ በተባለው የሩሲያ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ኤንጅልስ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ ዝቅ ብሎ ይበር እንደነበርና በአደጋው ከሞቱት መካከል ሶስቱ የጦር ሰፈሩ አባላት መሆናቸውን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ትናንት እሁድ በቪዲዮ ባስተላለፉት የመልካም ገና በዓል መልዕከታቸው የዩክሬንን ተከላካዮች አመስግነዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው “አንድ ጊዜ ሁላችንም ዛሬ በዚች ቀንና በሌሌች ቀናትም ሁላችንም አብረን መኖር እንድችል የቻሉትን ሁሉእየሰሩ ያሉትን በሙሉ በጋራ እንድናመሰግናቸው እፈልጋለሁ” ብለዋል።

ዜለነስኪ አክለው እውነቱን እያሰራጩ ያሉትን ጋዜጠኞች፣ መሪዎች እና በመላው ዓለም ዩክሬንን የሚደግፉትን ሰዎች አመስግነዋል።

ይሁን እንጂ አሉ ዜለነስኪ “በዚህ ዓመት ሁሉን ነገር አጥታ ሊሆን ይችላል ያሏትን ሩሲያ ኪሳራዋን ለማካካስ በአገራችንና በኃይል አቅርቦታችን ላይ እያደረገች ያለውን የሮኬት ጥቃት የፕሮፖጋንዳ ሰዎችዋ በኩራት እንዲያስተጋቡ እየሞከረች ነው " ብለዋል።

“ ያለመብራት" ጨለማ ውስጥ መሆናችን ወራሪዎችን ወደ አዲሱ ሽንፈታቸው እንዲያመሩ ከማድረግ አያግደንም” ያሉት ዜለነስኪ “ይሁን እንጂ ለማናቸውም ዓይነት ሁኔታ መዘጋጀት ይኖርብናል” በማለት ጥንቃቄን አሳስበዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን “ሩሲያ1 ስቴት” ለተባለ ቴሌቭዥን ጣቢያ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ይቺ አገር በዩክሬን ጦርነት ከተሳተፉ ወገኖች ጋር ሁሉ ለመደራደር ዝግጁ ናት ይሁን እንጂ ኪቭ እና ምዕራባውያን ደጋፊዎችዋ መነጋገር አልፈለጉም” ብለዋል።

እኤአ የካቲት 24 ዩክሬንን የወረረው ክሬምሊን የታቀደው ዓላማ ግቡን እስኪመታ ድረስ የሚዋጋ መሆኑን ሲገልጽ ኪቭም በበኩሏ ሩሲያ እኤአ በ2014 የጠቀለለቻትን ክሬሚያን ጨምሮ ሁሉም የሩሲያ ወታደር ከዩክሬን ግዛቶች ተጠራርጎ እስኪወጣ ድረስ ውጊያውን እንዳማታቆም አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG