በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክርስትና ዕምነት አማኞች ገናን በቤተልሄም አከበሩ



የክርስትና ዕምነት አማኞች ገናን በቤተልሄም አከበሩ
የክርስትና ዕምነት አማኞች ገናን በቤተልሄም አከበሩ

ከመላ ዓለም የመጡ የክርስትና ዕምነት አማኞች እና ጎብኝዎች በቤተልሄም በመገኘት የእየሱስ ክርስቶስን ልደት ሲያከብሩ ውለዋል።የጎብኝዎች እና ምዕመናኑ ቁጥር ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ገና ባያስተካከልም ሆቴሎች ምግብ ቤቶች ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ላይ በደንበኞች መያዛቸውን ተከትሎ ለዌስት ባንክ የኢኮኖሚ ጉልበት ይሆናል ተብሎ ተጠብቋል።

ከሁለት ዓመት ኮቪድ-ነክ የእንቅስቃሴ ገደብ በኃላ የቤተልሄም መንገዶች ዳግም በገና ቀን በህዝብ ተሞልተዋል። ይሁንና የፍልስጤማዊያን ክርስቲያኖች ቁጥር ግን እየቀነሰ እንደመጣ ተዘግቧል።

እየሱስ ክርስቶስ እንደተወለደበት በሚነገርበት ስፍራ ላይ የቆመውን ቤተክርስቲያን የሞሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመላ ዓለም በተላለፈው የእኩለ ሌሊት ልዩ ስነ-ስርዓት ላይ ተካፋይ ሆነዋል።የፍልስጤማዊያኑ ፕሬዚደንት መሐሙድ አባስን ጨምሮ ባለስልጣናት በቤተልሄም የነበረውን ስነስርዓት ታድመዋል።

የላቲን ፓትሪያሪክ ፔርባቲስታ ፒዛቤላ ዓለም በክብር እና ነጻነት ለመኖር ለሚጠባበቁ ለፍልስጤማዊያን ትኩረት አለመስጡትን ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታም እየኖሩ እንደሆነ አውስተዋል። የልደት በዓል መልዕክት ሰላም እንደሆነም አክለዋል።

የአሁኑ የገና በዓል የተከበረው በዌስት ባንክ የሚገኘው የፍልስጤማዊያን ቁጥር ከመላው ነዋሪ ጋር ሲነጻጸር ከ1 በመቶ በወረደበት ወቅት ነው።

ሀኒ አል ሃይቅ የተባሉት አሁንም ክርስቲያኖች በብዛት ከሚኖሩባቸው የዌስት ባንክ ስፍራዎች አንዱ የሆነው የቤተ ሳሁር ከንቲባ ፣ በስፍራው ነዋሪ የሆኑ ክርስቲያኖች ቁጥር የበለጠ እንዳያሽቆለቁል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በአካባቢው ባለው የሰላም እና ደህነነት ዕጦት ምክንያት በርካታ ነዋሪዎች ወደ ሌሎች ሀገራት እየተሰደዱ እንደ ሆነም ጠቁመዋል። በቀጠለው የፍልስጤማዊያን እና እስራኤላዊያን ግጭት እስካሁን 150 ፍልስጤማዊያን መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ቢሮ ይገልጻል ። በ16 ዓመታት ውስጥ ብዙ ሰው የረገፈበት ግጭት ነውም ተብሏል። 20 እስራኤላዊያን በዚህ ግጭት አልቀዋል። አብዛኞቹ የተገደሉት ፍልስጤማዊያን ወታደሮችን ያጠቁ ታጣቂዎች እንደሆኑ እስራኤል ትሟገታለች ።

XS
SM
MD
LG