በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ትርጉም- የለሹ" የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሮማ ሊቀ-ጳጳስ በገና መልዕክታቸው አሳሰቡ


"ትርጉም የለሹ" የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሮማ ሊቀ-ጳጳስ በገና መልዕክታቸው አሳሰቡ
"ትርጉም የለሹ" የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም የሮማ ሊቀ-ጳጳስ በገና መልዕክታቸው አሳሰቡ

የሮማ ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ፣ ከቫቲካን ባስተላለፉት የገና በዓል መልዕክታቸው በዩክሬን ያለው "ትርጉም -የለሽ" ጦርነት እንዲቆም ተማጽነዋል ።

የ86 ዓመቱ ሊቀ-ጳጳስ 10 ወራትን ያስቆጠረው ግጭት በመላ ዓለም ላይ የምግብ እጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ "ምግብን በመሳሪያነት" መጠቀም ይቆም ዘንድ አሳስበዋል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ይሄንን መልዕክታቸውን ያሰሙት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ነው።ከምዕመናኑ መካከል የተወሰኑት ዬክሬንን ሰንደቅ ዓለማ ይዘው ታይተዋል።ሊቀ-ጳጳሱ በማስከተል ቡራኬ ሰጥተዋል ።

ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ በየካቲት ወር ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ቀን አንስቶ ጦርነቱን በማውገዝ ከሩሲያ ጋር ያለው ደካማ ተግባቦት ለመጠገን ጥረት ሲያደርጉ ሰንብተዋል፥።

የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል ሰገነት ላይ ሆነው ባሰሙት መልዕክታቸው "ይሄንን የገና በዓል በጨለማ እና በቅዝቃዜ ከቤታቸው ርቀው የሚያሳልፉ " ፣ ላሏቸው ዩክሬናዊያን ወንድም እና እህቶች የማጽናኛ መልዕክት ከመስደዳቸው በተጨማሪ ፣ በጦርነቱ ለተጎዱ ሁሉ የጋራ የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግም አሳስበዋል።

ሊቀ-ጳጳሱ በንግግራቸው በግጭትም ሆነ በሌሎች ቀውሶች ውስጥ የሚገኙ ፣ ከአፍጋኒስታን እስከ የመን ፣ ሶሪያ ፣ ማይንማር ፣ የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ፣ ሊባኖስ እና ሄቲ አንስተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ በሴቶች በተመራ ተቃውሞ ላለፉት ሶስት ወራት በመናጥ ላይ ባለችው ኢራን ውስጥ እርቅ እንዲፈጠርም ጥሪ አቅርበዋል።

የገናን በዓል የሚያከብሩ ሁሉ፣ በየቀኑ ብዙ መጠን ያለው ምግብ ከጥቅም ውጭ በሚሆንበት ፣ ሀብት ለጦር መሳሪያ መግዣ በሚፈስበት በአሁኑ ወቅት ፣ የተረቡትንም እንዲያስቡ አሳስበዋል። ዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው።

XS
SM
MD
LG