በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከባድ የክረምት አየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ አወጣች


በሚኒያፖሊስ ቻርልስ ዛጂክ የተሰኘ ግለሰብ በመረማመጃ መንገድ ላይ የተከማቸውን በረዶ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መጥረጊያ ተጠቅሞ ያፀዳል - ታህሳስ 22, 2022
በሚኒያፖሊስ ቻርልስ ዛጂክ የተሰኘ ግለሰብ በመረማመጃ መንገድ ላይ የተከማቸውን በረዶ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መጥረጊያ ተጠቅሞ ያፀዳል - ታህሳስ 22, 2022

በዩናይትድ ስቴትስ አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው ለህይወት አስጊ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እና አደገኛ የንፋስ ቅዝቃዜ "መንቀሳቀስ ላልቻሉ መንገደኞች፣ ከቤት ውጪ ለሚሰሩ ግለሰቦች፣ ከብቶች እና የቤት ውስጥ እንስሳት" ህይወት አስጊ ነው ሲል የሀገሪቱ ብሄራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ዛሬ አስታወቀ።


"መጓዝ ካለባችሁ ወይም ወደ ውጪ የሚያስወጣ ጉዳይ ካላችሁ፣ ተደራራቢ ልብስ በመልበስ፣ ሙሉ የሰውነታችሁን ቆዳ በተቻለ መጠን በመሸፈን እና ለክረምት የሚያገለግሉ የደህንነት እቃዎችን በመኪናችሁ በማስቀመጥ" ለከፍተኛ ቅዝቃዜው ተዘጋጁ ሲል የአየር አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአንዳንድ አካባብዊዎች ከቤት ውጪ መሆን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ በረዶነት ወደሚቀየር አየር ሊያጋልጥ እንደሚችልም አመልክቷል።

በአሜሪካ መሰረታዊ አገልግሎቶችን አጠቃቀም የሚከታተለው 'ፓወር አውትሬጅ' የተሰኘ ድህረገፅ እንዳስታወቀው፣ የኃይል መቆራረጥ ወደ 1.4 ሚሊየን መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማጥ በጭለማ እንዲዋጡ አድርጓል።

በቴኔሲ ግዛት የሚገኘው ትልቁ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት አቅራቢ ተቋም የጠፋው መብራት አርብ እለት ምሽት መመለሱን ቢያስታውቅም፣ ህብረተሰቡ ኃይል እንዲቆጥብ ግን አሳስቧል። በጆርጂያ ክፍለግዛት፣ በአትላንታ እና በሰሜናዊው የግዛቱ አካባቢ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም እንዲሁ መብራት ያልነበራቸው ሲሆን ያለ ሙቀት ከዜሮ በታች ወደ ሆነ የንፋስ ቅዝቃዜ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

በተጨማሪም 'ፍላይት አዌር' የተሰኘው በረራዎችን የሚከታተል ድህረገፅ አርብ እለት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እና ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ የሚደረጉ ወደ 5ሺህ የሚጠጉ በረራዎች በቅዝቃዜው ምክንያት መሰረዛቸውን አስታውቋል። ይህም በርካታ መንገደኞች ነገ ለሚከበረው የገና በዓል ወደ ቤታቸው መሄድ እንዳይችሉ አስተጓሉሏቸዋል።


ወደ ሞቃታማ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተገፋ የሄደው የአርክቲክ አየር በምስራቃዊው የአሜሪካ ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨ ሲሆን የሙቀት መጠኑ ከ25 እስከ 35 ዲግሪ ከአማካዩ በታች እንደሚሆን የአየር ሁኔታ አገልግሎቱ ጨምሮ አስጠንቅቋል።

XS
SM
MD
LG