በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናታንያሁ የጥምር መንግስት መሠረቱ


ፋይል - ቤንጃሚን ናታንያሁ በእየሩሳሌም ንግግር ሲያደርጉ - ህዳር 2, 2022.
ፋይል - ቤንጃሚን ናታንያሁ በእየሩሳሌም ንግግር ሲያደርጉ - ህዳር 2, 2022.

በእስራኤል ለረጅም ግዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ቤንጃሚን ናታንያሁ የጥምር መንግስት መመሥረታቸውን አስታውቀዋል።

የጥምር መንግስቱ ወግ አጥባቂዎችንና አክራሪ ኦርቶዶክስ ፓርቲዎችን ያካተተ መሆኑ ታውቋል።

በአዲሱ መንግስት የተካተቱት በርካታ ሚኒስትሮች የዌስት ባምክን ሰፊ ግዛትን ለመጠቅለል እንዲሁም ‘ተምፕል ማውንት’ በተባለው ሥፍራ የአይሁድ ጸሎት እንዲከናወን እንደሚፈልጉ ታውቋል። ይህም ከሙስሊሞች እንዲሁም ከአሜሪካ ጋር እስራኤልን ውጥረት ውስጥ ሊከት ይችላል ተብሏል።

አሜሪካ በዌስት ባንክ፣ ጋዛ እና ምሥራቅ እየሩሳሌም ላይ ያላት አቋም ቦታዎቹ የፍልስጤም አካል መሆን አለባቸው የሚል ነው።

ናታንያሁ መንግስት መመሥረታቸውን ለፕሬዝደንት አይሳክ ሄርዞግ ደውለው ያስታወቁት የመመሥረቻው ቀነ ገድብ ሊያልቅ 20 ደቂቃ ሲቀረው እንደነበር የቪኦኤዋ ሊንዳ ግራድስታይን ከእየሩሳሌም የላከችው ዘገባ አመልክቷል።

አዲሱ መንግስት የተመሠረተው እስራኤል በአራት አመት ውስጥ ለአምስተኛ ግዜ ካደረገችው ያለፈው ምርጫ ሰባት ሳምንት በኋላ መሆኑ ነው።

ናታንያሁ መንግስታቸውን የመሠረቱት በበርካታ ሙስና ክሶች ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ባሉበት ወቅት ሲሆን ናታንያሁ ውንጀላውን ሁሉ ያስተባብላሉ።

XS
SM
MD
LG