በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ
አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ

የኦሮሞ ገዳ ስርዓትን ለዓለም በማስተዋወቅ ቀዳሚ ከሆኑት አንዱ እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ ባደረባቸዉ ህመም ሲረዱ ቆይተዉ ትላንት በሚኖሩበት ሻኪሶ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን የጉጂ ዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ የኦሮሞ ገዳ ስርዓት አርአያ በመሆን በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲወርድ ሲተጉ የነበሩ ሰዉ ናቸዉ ሲሉ የዞኑ ባህልና ቱርዝም ኃላፊ የሆኑት አቶ አዱላ ሚዔሳ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በ1992 የገዳን በትረስልጣን የተረከቡት ዓጋ ጤንጠኖ በጉጂ ገዳ ስርዓት 72 ኛዉ አባ ገዳ የነበሩ ሲሆን የገዳ ስርዓት እንዲጠና እና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እውቅና እንዲያገኝ በማድረግ ለሕዝብ ያስተዋወቁ መሪ መሆናቸው ተገጿል።

አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ በሕይወት ዘመናቸዉ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክቴሬት ያገኙ ሲሆን በቅርብ ጊዜ በተቋቋመው የገዳ ጥናትና ምርምር ተቋም ዉስጥም በአማካሪነት ያገለግሉ ነበር። ትላንት ሐሙስ በ78 አመታቸዉ ማረፋቸዉ የተነገረዉ አባ ገዳ ዓጋ ጤንጠኖ በመጪው እሁድ የቀብር ስነስራታቸዉ በሻኪሶ እንደሚፈፀም ሃላፊው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG