በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምስራቅ ኬንያ በአል-ሻባብ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ፖሊስ እና ሌላ ሲቪል ተገደሉ


ፋይል - አንድ የኬንያ ፖሊስ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ፣ ኢስሊ አካባቢ ከተጣለው የሰዓት እላፊ በኃላ ወደ ቤቱ የሚጓዝን አንድ ሰው አቁሞ ሲያነጋግር
ፋይል - አንድ የኬንያ ፖሊስ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ፣ ኢስሊ አካባቢ ከተጣለው የሰዓት እላፊ በኃላ ወደ ቤቱ የሚጓዝን አንድ ሰው አቁሞ ሲያነጋግር

በምሥራቅ ኬንያ ከሶማሊያ ጋር በምትዋሰነው ጋሪሳ በተባለች ስፍራ ትናንት ለተገደሉት አንድ የፖሊስ አባልና አንድ ሲቪል ተጠያቂው አል-ሻባብ ነው ሲል የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ አህመድ ሁሴን ከስፍራው እንደዘገበው ስድስት ሰዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የፖሊስ መኪና የተቀበረ ፈንጂ ላይ ሲወጣ ሁለቱ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል።

አዛዡ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደነገሩት የተጎዱ ሌሎች ሶስት ሰዎች በሄሊኮፕተር ወደ መዲናዋ ናይሮቢ ለህክምና ተወስደዋል።

ከጥቃቱ ጀርባ አል-ሻባብ እንዳለና አንድ የጸጥታ ቡድንም የቡድኑን ተዋጊዎች በማሰስ ላይ መሆናቸው አዛዡ ገልፀዋል።

የትናንቱ ጥቃቱ የመጣው በአል-ሻባብ ሳይፈጸም አይቀርም በተባለ ሌላ ጥቃት በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የሚገኝ የሬዲዮ መገናኛ አንቴና ከጥቂት ቀናት በፊት ከወደመ በኋላ ነው።

ኬንያ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር የሚያገለግል ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ከላከች ጀምሮ፣ መሠረቱን በሶማሊያ ያደረገው አል-ሻባብ በኬንያ ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

XS
SM
MD
LG