የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት የሚገመግመውና የሚከታተለው የአፍሪካ ኅብረት ቡድን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት መቀሌ እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪዎች ቡድን ጠቆመ።
የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ትላንትናና ዛሬ ለሁለት ቀናት በናይሮቢ ያደረጉትን ሁለተኛ ዙር ውይይት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የአደራዳሪ ቡድኑ አባል የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ቡድኑ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ወደ መቀሌ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የስምምነቱን ተግባራዊነት የሚከታተለው የአፍሪካ ኅብረት ቡድን ሙሉ ተደራሽነት እንዲኖረው ስምምነት ላይ መደረሱም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ከትላንት ጀምሮ ግጭት በማቆም ስምምነቱ አተገባበር ዙሪያ በናይሮቢ ያደረጉት ውይይት ባለፈው ኅዳር ያካሔዱት ውይይት ተከታይ ነው፡፡
ይሄው ውይይት መጠናቀቁን በማስመልከት በተሰጠው መግለጫ ላይ፣ የሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ አዛዦች ባይገኙም ስምምነት ተደረሱባቸው የተባሉ ነጥቦች በአገራዳሪዎች በኩል ተብራርተዋል፡፡
የአሁኑ ውይይት በተለይ የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም፣ ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሱት የኬንያው ፕሬዝደንት ኬንያታ፣ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተጓዙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ /ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/