በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ኮንጎ ያለው ውጊያ አገርሽቷል


ፋይል - የአርበኞች ህብረት ለነጻ እና ገለልተኛ ኮንጎ የተሰኘው ሚሊሺያ አባላት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚገኘው ኪትሻንጋ ቅኝት ሲያደርጉ ታህሳስ 11, 2022
ፋይል - የአርበኞች ህብረት ለነጻ እና ገለልተኛ ኮንጎ የተሰኘው ሚሊሺያ አባላት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚገኘው ኪትሻንጋ ቅኝት ሲያደርጉ ታህሳስ 11, 2022

ከቀናቶች ፋታ በኋላ በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በኤም-23 አማጽያንና በተፎካካሪ ሚሊሺያ መከከል ዛሬ ውጊያ አገርሽቷል።

እንደ ኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ ከሆነ ‘የአርበኞች ኅብረት ለነጻና ሉአላዊ ኮንጎ’ የተሰኘው ሚሊሺያ በሰሜን ኪቩ ክልል ጦርነት መቀስቀሱን አስታውቋል።

የህንብረቱ አዛዥ በውጊያ ላይ መሆናቸውን ሲናገሩ፣ የኅብረቱ ቃል አቀባይ ደግሞ ከ ኤም-23 ጋር ግጭት ማገርሸቱን ገልጸዋል።

ኅብረቱ ‘ሁንዴ’ የተሰኘውን ጎሳ እንደሚወክል አስታውቆ፣ በሰሜን ኪቩ ክልል ሰፊ ግዛትን የተቆጣጠረውን ኤም-23ን ለማጥፋት መነሳቱን ይናገራል።


በቱትሲ የሚመራው ኤም-23 በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሚገኙና በደርዘን ከሚቆጠሩ አማጺያን አንዱ ነው።

የኮንጎ መንግስት ተዋጊዎቼን በሠራዊቱ ውስጥ አላካተተም በሚል ኤም-23 ከረዥም ግዜ ዝምታ በኋላ ባለፈው ዓመት መሣሪያውን እንደገና አንስቷል።


ኮንጎ ጎረቤቷን ሩዋንዳ ኤም-23ትን ትደግፋለች ስትል የምትከስ ሲሆን ሩዋንዳ በተደጋጋሚ ክሱን አስተባብላለች።

የአሜሪካ፣ ፈረንሳይ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች ግን ክሱ እውነትነት አለው ባይ ናቸው።

XS
SM
MD
LG