በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን በሴቶች ላይ የሚያደርሰው በደል አሜሪካንን አሳስቧል


ፋይል - የታሊባን አባላት በካቡል ዩንቨስቲ መግቢያ ላይ ቆመው ሲጠብቁ ታህሳስ 21, 2022.
ፋይል - የታሊባን አባላት በካቡል ዩንቨስቲ መግቢያ ላይ ቆመው ሲጠብቁ ታህሳስ 21, 2022.

ሴቶች ትምህርት እንዳይማሩ ባገደው የአፍጋኒስታኑ ታሊባን ላይ አሜሪካ ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያጤነች ነው ሲሉ አንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት ተናገሩ።

በአፍጋኒስታን የአሜሪካ ዲፕሎማቲክ ልዑክ ሃላፊ ኬረን ዴከር ትናንት ማምሻዉን ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት፣ ታሊባን በአገሪቱ በሚገኙ የመንግስትም ሆነ የግል ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ ሴቶች መታገዳቸውን ባሳወቀ ማግስት ነው።

ዲፕሎማቷ ኬረን ካታር ላይ ሆነው እንደተናገሩት፣ በዋሽንግተን የሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤታቸው፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት፣ የሚወሰዱትን እርምጃዎች እያጤነ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ ጦር ከ20 ዓመታት በኋላ አምና ከአፍጋኒስታን ለቆ ከወጣ በኋላ ታሊባን አገሪቱን ሲቆጣጠር አሜሪካና ሌሎች የምዕራብ አገራት ካታርን እንደ ዲፕሎማሲ ማዕከላቸው በመጠቀም ላይ ናቸው።

በአፍጋኒስታን በወንዶች ብቻ የተዋቀረው የታሊባን አስተዳደር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በተለይም በሴቶች ላይ ያለው አያያዝ አሳሳቢ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕጋዊ እውቅና ከመስጠት ተቆጥቧል።

XS
SM
MD
LG