በየመን ለስምንት ዓመታት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች የያዟቸውን በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች መጎብኘቱን ቀይ መስቀል ዛሬ አስታውቋል። ጉብኝቱ ለእስረኞች ልውውጥ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል ተብሏል።
የቀይ መስቀል የቀጠናው ሀላፊ ለአሶስዬትድ ፕረስ እንደገለጹት፣ የድርጅቱ አባላት ለ 10 ቀናት በሳዑዲ አረቢያና በየመን ባደረጉት ጉብኝት 3ሺ400 የሚሆኑ እስረኞች ተመልክተዋል።
በዓለም አስከፊ ቀውስን ያስከተለ ነው በተባለው በየመኑ ግጭት ከ 150ሺህ ሰዎች በላይ አልቀዋል።
ሁለቱም ወገኖች ስለያዙት የእስረኛ ቁጥር ብዛት አያስታውቁም። በጦርነቱ ወቅት ግን በ10ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተያዙ ይገመታል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።