በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ክልል ተወካዮች በናይሮቢ ስብሰባ ተቀምጠዋል


ፋይል - በስተግራ የሚታዩት የትግራይ ኃይሎች መሪ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኃላፊ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በናይሮቢ የተደረሰውን ስምምነት ሲያነቡ Nov. 12, 2022
ፋይል - በስተግራ የሚታዩት የትግራይ ኃይሎች መሪ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኃላፊ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በናይሮቢ የተደረሰውን ስምምነት ሲያነቡ Nov. 12, 2022

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ባለስልጣናትና እና የትግራይ ክልል ተወካዮች ቀጣይ የሰላም ስምምነቱን ሂደቶች በተመለከተ ንግግር ለማድረግ በኬንያ መዲና ናይሮቢ እንደተገናኙ ተሰምቷል።

የአሜሪካ ድምፁ ሞሃመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ከላከው ዘገባ መረዳት እንደተቻለው፣ ሁለቱ ወገኖች ለንግግር የተቀመጡት፣ “በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ ሆኗል፣ ምክንያቱም የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በክልሉ በመገኘታቸው ነው” በማለት የትግራዩ ወገን ክስ በሚያቀርብበት ወቅት ነው።

“የክልልሉ ባለስልጣን አትንኩት መዝገቡ የኤርትራ ወታደሮች በሲቪሎች ላይ ያደርሳል ያሉትን ጥቃትና ዘረፋ በተመለከተ የፌዴራሉ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል” ሲሉ ለትግራይ የሚወግኑ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸውን የሞሃመድ ዩሱፍ ሪፖርት አመልክቷል።

በመቀጠል ላይ ነው የተባለው ግጭት የሰላም ስምምነቱን እንዳያስተጓጉል ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሙያዎች ስጋት አድሮባቸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።

የሰላም ስምምነቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስና የስልክና ባንክ አገልግሉት እንዲቀጠል አስችሏል ሲል ሪፖርቱ አስታውሷል።

በአፋር በትግራይና በአማራ ክልልሎች ከ 8 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ ዕርዳታ አግኝተዋል ሲል የፌዴራሉ መንግስት አስታውቋል።

የሁለቱ ወገን መሪዎች የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በተከታታይ ሲገናኙ ቆይተዋል።

ዛሬ ናይሮቢ የተጀመረው ስብሰባ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG