በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ተዋጊ ሃይሏን ወደ 1.5 ሚሊዮን ልታሳድግ ነው፣ አዲስ ሚሳዬልም ልትታጠቅ ነው


ይህ ምስል ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው ወታደራዊ ጥቃት የተጎዳ የመኖሪያ ህንፃን ያሳያል።
ይህ ምስል ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው ወታደራዊ ጥቃት የተጎዳ የመኖሪያ ህንፃን ያሳያል።

በሩሲያ ጦር ውስጥ ያለውን ተዋጊ ሃይል ወደ 1.5 ሚሊዮን መጨመር እንደሚያስፈልግ የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር ሃሳብ አቅርበዋል። ፑቲን በበኩላቸው አገራቸው በሚቀጥለው ወር በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው ያሉትን “ዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬል” እነደምትታጠቅ ይፋ አድርገዋል።

“695ሺህ የኮንትራት ወታደሮችን ጨምሮ የሩሲያን ተዋጊ ሃይል ወደ 1.5 ሚሊዮን ማሳደግ አስፈላጊ ነው፣” ሲሉ በአንድ ስብሰባ ላይ መከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ ለፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሃሳብ አቅርበዋል። ፑቲንም በሃሳቡ ተስማምተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት “በጋራ የፈጸምነው አሳዛኝ ድርጊት” ቢሆንም ተጠያቂዎቹ ዩክሬንና አጋሮቿ ናቸው ሲሉ ፑቲን ዛሬ ተናግረዋል።

“የእኛ ፖሊሲ ውጤት ሳይሆን፣ የሶስተኛ አገራት ፖሊሲ ውጤት ነው” ሲሉ በአገሪቱ ቴሊቭዥን በቀጥታ በተላለፈና ከከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ተናግረዋል።

ፑቲን በዚሁ ስብሰባ ላይ የሩሲያን የውጊያ ብቃት ማሳደጋቸውን እንድሚቀጥሉና ይህም የኑክሌር ሃይል ዝግጁነትን ማሻሻል እንደሚያካትት ተናግረዋል።

በሚቀጥለው የአውሮፓውያን ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያ “ዚሮን ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬል” እነደምትታጠቅ እና ይህም በዓለም ተወዳዳሪ እንደልለው ፑቲን ጨምረው ይፋ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG