በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ ዋሽንግተንን ሊጉበኙ ነው


ዩክሬን/ዩናይትድ ስቴትስ
ዩክሬን/ዩናይትድ ስቴትስ

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ዋሽንግተንን ለመጎብኘት በጉዞ ላይ ናቸው። በጉብኝታቸውም በኋይት ሃውስ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ከካቢኔያቸው እና ከብሄራዊ የጸጥታ ቡድናቸው ጋር እንድሚገናኙ ይጠበቃል። በተጨማሪም ለሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤቶች፣ ማለትም ለህግ አውጪው እና ለተወካዮች ም/ቤት በጋራ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ሩሲያ አገራቸውን ከወረረች ወዲህ ዜሌኒስኪ ወደ ውጪ ጉዞ ሲያደርጉ የመጀመሪያው ነው።

ፕሬዝደንት ዜሌንስኪ ዛሬ በማለዳ በላኩት የትዊተር መልዕክት ወደ አሜሪካ በመጓዝ ላይ መሆናቸውንና ዓላማውም የዩክሬንን የመከላከያ አቅም ለማጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል።

አንድ የባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት፣ ዜለንስኪ ወደ አሜሪካ ያቀኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ነው።

ባለሥልጣኑ እንዳሉት ዜሌንስኪ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በሚያደርጉት ውይይት፣ በጦር ሜዳ ስለሚኖረው የወደፊት ስልት በጥልቀት ይወያያሉ። በተጨማሪም አሜሪካና አጋሮቿ ማቅረብ ስለሚገባቸው የጦር መሣሪያዎች እንዲሁም ስልጠና ይነጋገራሉ።

ከሩሲያ የሚመጣውን የሚሳይልና የድሮን ጥቃት ለመመከት አሜሪካና አጋሮቿ የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎችን እንዲያቀርቡላቸው ዜሌንስኪ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ሰንብተዋል።

XS
SM
MD
LG