No media source currently available
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ የቀድሞ ፕሬዚደንት በወንጀል እንዲከሰሱ ጠየቀ። እንደ አውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ጥር 6 /2021 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚመረምረው ኮሚቴ ፤ የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ አመጹን ያካሄዱትን መርዳትን ጨምሮ አራት የወንጀል ክሶች እንዲመሰረቱባቸው ጠይቋል። ዘገባውን ያጠናቀረችው የቪኦኤ ምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን ናት።