በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሜሲ የኢንስታግራም ሪከርድ ሰበረ

በካታር እ.አ.አ የ2022 ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያ ከፈርንሳይ ጋር የተጫወተው አርጀንቲና ካሸነፈ በዋላ፣ የአርጀንቲና አምበል ሊዎኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫውን ይዞ ከደጋፊዎቹ ጋር ሲያከብር
በካታር እ.አ.አ የ2022 ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያ ከፈርንሳይ ጋር የተጫወተው አርጀንቲና ካሸነፈ በዋላ፣ የአርጀንቲና አምበል ሊዎኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫውን ይዞ ከደጋፊዎቹ ጋር ሲያከብር

የአርጀንቲና ቡድን አምበልና ኮከብ ተጫዋች ሊዎኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫውን ይዞ ከቡድኑ አባላት ጋር የተነሳውን ፎቶ በኢንስታግራም ካጋራ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኩ ታሪክ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኘ ፎቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ65 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያው ቋንቋ፣ ‘ላይክ’ አድርገውታል።

ሜሲ “የዓለም ሻምፒዮኖች!!!” ከሚል ፅሁፍ ጋር ባጋራው መልዕክት ይህን ወቅት ሁሌም ያልመው እንደነበርና፣ አሁንም ገና እውነት እንደማይመስለው ጨምሮ ገልጿል።

ሜሲ የኢንስታግራም ሪከርዱን የሰበረው "ወርልድ ሪከርድ ኤግ" የተሰኘ ገፅ እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም አጋርቶት የነበረው የእንቁላል ፎቶ አግኝቶት የነበረውን ከ56 ሚሊየን በላይ 'ላይክ' በመብለጡ ነው።

XS
SM
MD
LG