በጀርመን የሚገኝ ፍ/ቤት አንዲት የ97 ዓመት ሴት በአንድ የናዚ ማጎሪያ ሥፍራ ለተጨፈጨፉና ከአስር ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋት ላደረጉት ተሳትፎ በአመክሮ የሚታይ የሁለት ዓመት የእሥር ቅጣት አስተላልፏል።
ኢርምጋርድ ፉርችነር የተባሉት ሴት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በስተቶፍ ናዚ ማጎሪያ ካምፕ ፀሃፊ ነበሩ።
የካምፑ ሃላፊዎች ከእ.አ.አ1943 እስከ 1945 ለፈጸሙት ጭፍጨፋ ተባባሪ ነበሩ በሚል ተከሰው ነበር።
የመከላከያ ጠበቆቻቸው ከሳሽ ግለሰቧ ግድያው ይከናወን እንደነበር ማወቃቸውን በማያጠራጥር መንገድ አላረጋገጠም ሲሉ ተሟግተዋል።
ግለሰቧ በፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ቀን ይቅርታ ጠይቀው፣ በካምፑ በመገኘታቸው ተጸጽተዋል።
አሁን ፖላንድ ተብላ በምትጠራው አገር በነበረ ካምፕ ውስጥ 65 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል።
የፍርድ ሂደቱ በጀርመን ሁለተኛው የዓለም ጦርነትን በተመለከተ ከሚደረጉት የፍ/ቤት ክሶች ከመጨረሻዎቹ አንዱ ነው ተብሏል።