በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ኑክሌር ጣይ ተዋጊ አውሮፕላኖቿን በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ አበረረች


የዩናይትድ ስቴትስ ቢ-52 እና ሲ-17 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶች በኮሪያ የጋራ ልምምድ ወቅት ሲበሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ቢ-52 እና ሲ-17 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶች በኮሪያ የጋራ ልምምድ ወቅት ሲበሩ

ዩናይትድ ስቴትስ ኑውክሌር የመሸከም አቅም ያላቸውን ቢ-52 ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ዛሬ በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ ለልምምድ አብርራለች። ይህም ከሰሜን ኮሪያ ሊመጣ የሚችልን ስጋት የመመከት አቅሟን ለማሳየት ነው ተብሏል። በተጨማሪም ኤፍ-22 የተባሉትን ስቲልዝ ተዋጊ ጄትችንም ማብረሯ ተሰምቷል።

ደቡብ ኮሪያ ብበኩሏ ኤፍ-35ኤ እና ኤፍ-15ኬ ይተሰኙ ተዋጊ ጄቶቿን በልምምዱ ማሳተፏን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ልምምዱን ያደረጉት በዚህ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሳዬል ሙከራ ላደረገችውና በአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ላይ ዛቻዋ እየጨመረ ለመጣው ሰሜን ኮሪያ ጡንቻቸውን ለማሳየት ነው ተብሏል።

ሁለቱ አገሮች ወታደራዊ ልምምዳቸውን ለማጠናከርና በአሜሪካ በኩል የሚቀርቡትን የመሣሪያና ጄቶችን ቁጥር ለመጨመር፣ እንዲሁም አሜሪካ ደቡብ ኮሪያን ለመከላከል የገባቸውን ቃል በተግባር እንድታጠናክር ባለፈው ወር ተስማምተው ነበር።

የደቡብ ኮሪያው የመከላከያ ሚኒስቴር ያንን ስምምነት በመጥቀስ፣ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳዬል ዛቻ መልስ ለመስጠት ሁለቱ አጋሮች የመከላከያ ብቃታቸውን ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ ሲል በመግለጫው ማስታወቁን የቪኦኤው ዊሊያም ጋሎ ከሶል ዘግቧል።

ሰሜን ኮሪያ መካከለኛ ርቀት ያላቸውን ባሊስቲክ ሁለት ሚሳዬሎች ከቀናት በፊት አስወንጭፋለች። የመጀመሪያውን የስለላ ሳተላይት ለመላክም ወሳኝና የመጨረሻ ሙከራ ነው ብላለች።

XS
SM
MD
LG