በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ የእስላሚክ ስቴት አባላት ናቸው የተባሉ 17 ግለሰቦች በሞት ተቀጡ


የሊቢያን ዋና ከተማ ትሪፖሊን የሚያሳይ ካርታ
የሊቢያን ዋና ከተማ ትሪፖሊን የሚያሳይ ካርታ

እስላሚክ ስቴት ወይም አይ.ኤስ በሚል ምጻረ ቃል የሚታወቀውን አክራሪ ቡድን ተቀላቅላችኋል የተባሉ 17 ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ትሪፖሊ የሚገኝ ፍ/ቤት ወስኗል።

አቃቤ ሕግ እንደሚለው ግለሰቦቹ ግድያና ሌሎች ሰቆቃዎችን ፈጽመዋል። የመንግስትንም ሆነ የህብረተሰቡን ሰላም አውከዋል፣ በትጥቅ የታገዘ ሁከትም ፈጽመዋል።

ሁለት ሌሎች ሰዎች በእድሜ ልክ እስራት ሲቀጡ፣ 14 የሚሆኑ ደግሞ በተለያየ የእስራት ግዜ ተቀጥተዋል።

ተከሳሾቹ 53 ሰዎችን መግደላቸውን፣ ህንጻዎችን ማውደማቸውን እንዲሁም በርካታ ሰዎች እንዲሰወሩ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በሞት የተቀጡት ግለሰቦች ዜግነት ይፋ አልሆነም ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ በዘገባው አመልክቷል።

ከ11 ዓመታት በፊር የረጅም ዘመን መሪ የነበሩት ሞአመር ጋዳፊ በአመጽ ከስልጣን ተወግደው ከተገደሉ በኋላ፣ አይሲስን ጨምሮ በርካታ ቡድኖች በሚያደርጉት ግጭት ሊቢያ ትርምስ ውስጥ ትገኛለች።

ከ12 ዓመታት በፊት የሞት ቅጣት እንዲቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባኤ ውሳኔ ሲያሳልፍ ሊቢያ የተቃውሞ ድምጿን አስመዝግባለች። ምን ያህል የሞት ቅጣት እንደምትፈጽም ግን በይፋ አታሳውቅም።

XS
SM
MD
LG