በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታሊባን ጥፋት ፈጽመዋል የተባሉ በግርፋት ተቀጡ


ፋይል - የታሊባን የፀጥታ ኃይሎች በፓርዋን ግዛት ቻርካር ከተማ ሴቶች እና ወንዶች በአደባባይ ሲገረፉ የሚያዩ ሰዎችን ሲጠብቁ ይታያል
ፋይል - የታሊባን የፀጥታ ኃይሎች በፓርዋን ግዛት ቻርካር ከተማ ሴቶች እና ወንዶች በአደባባይ ሲገረፉ የሚያዩ ሰዎችን ሲጠብቁ ይታያል

በአፍጋኒስታን ሴቶችን ጨምሮ ከመቶ በላይ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች በአደባባይ በግርፋት መቀጣታቸውን ታሊባን አስታውቋል።

የታሊባን ጠቅላይ ፍ/ቤት ሴቶችን ጨምሮ 122 ግለሰቦች በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በስፖርት ስቴዲየም ውስጥ መገረፋቸውን አስታውቋል።

በትዳር ላይ በመማገጥ፣ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ ከቤት አምልጦ በመጥፋት፣ ሌብነትና አደንዛዥ እጽ በማዘዋዋር በሚል ከ 25 እስከ 30 ግዜ መገረፋቸውን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።

የታሊባን መሪዎች የሻሪያ ሕግ በሃገሪቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ባስተላለፉት ትዕዛዝ መሠረት የሞት ፍርድም ተፈጻሚ በመሆን ላይ ይገኛል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በአገሪቱ ምዕራባዊ ግዛት በአደባባይ የተፈጸመው የሞት ቅጣት፣ “ሰውን የገደለ በሞት ይቀጣ” የሚለውን እስላማዊ ሕግ መሠረት በማድረግ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለልተኛ ባለሙያዎች ቡድን በታሊባን እንደ አዲስ በመፈጸም ላይ ያለው ሕግ እያሳሰባቸው መሆኑን ዓርብ ዕለት አስታውቀው ነበር። “ኢሰብዓዊና ክብርን የሚነካ” ያሉት ቅጣት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG