በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔዘርላንድ በባሪያ ፍንገላ ላይ ለነበራት ድርሻ ይቅርታ ጠየቀች


ፋይል - የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ማርክ ሩተ እ.አ.አ March 19, 2020 በሄግ ሰጥተውት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ
ፋይል - የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ማርክ ሩተ እ.አ.አ March 19, 2020 በሄግ ሰጥተውት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ

የኔዘርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ አገራቸው በባሪያ ፍንገላ ላይ ለነበራት ድርሻ ዛሬ በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

“ዛሬ ይቅርታ እንጠይቃለን” ብለዋል ሩተ በብሄራዊ ሙዚየም ለሃያ ደቂቃዎች ባደረጉት ንግግር። ታዳሚው በጸጥታ ተቀምጦ ነበር ተብሏል።

አንዳንድ ማህበራዊ አንቂዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር አገሪቱ የባሪያ ፍንገላን ባገደችበት ቀን እንዲውል በሚል በሚቀጥለው ዓመት እንዲያደርጉት በፍርድ ቤት ጭምር ሞክረው ነበር። የሚቀጥለው ሐምሌ በአገሪቱ የባሪያ ፍንገላ የታገደበት 160ኛ ዓመት ይታወሳል።

አዋጁ ከወጣም በኋላ በባርነት የተያዙት አፍሪካውያን በየእርሻው እንዲሰሩ ተገደው ነበር በሚል ማህበራዊ አንቂዎች ትክክለኛው 150 ዓመት ነው በማለት እንደሚከራከሩ አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

በ17ኛው ክፍለ ዘመን ኔዘርላንድ 600ሺህ የሚሆኑ አፍሪካውያንን ወደ ካሪቢያን እና ደቡብ አሜሪካ በመውሰድ በባርነት እንዲያገለግሉ አድርጋለች።

በአገሪቱ መንግስት የተቋቋመ አማካሪ ቦርድ “በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኔዘርላንድ የተፈጸመው የባሪያ ፍንገላ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው” በማለት መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ ሃሳብ አቅርቦ ነበር።

ከአራት ዓመታት በፊት ዴንማርክ ጋናን ይቅርታ ስትጠይቅ፣ ቤልጂየም ደግሞ በኮንጎ ለተፈጸመው በደል መጸጸቷምን አስታውቃለች።

ከሰላሳ ዓመታት በፊት እ.አ.አ 1992፣ የወቅቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ዳግማዊ ጆን ፖል ቤተክርስቲያኒቷ በባሪያ ፍንገላ ላይ ለነበራት ድርሻ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG