በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላኩ ሕጋዊ ነው ሲል የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወሰነ


"ዘረኝነትን እንቃወም" የተሰኘው ዘመቻ ተሳታፊዎች ለንደን ከሚገኘው ፍርድቤት ውጪ መፈክሮችን ይዘው ይታያሉ Dec. 19, 2022.
"ዘረኝነትን እንቃወም" የተሰኘው ዘመቻ ተሳታፊዎች ለንደን ከሚገኘው ፍርድቤት ውጪ መፈክሮችን ይዘው ይታያሉ Dec. 19, 2022.

አጨቃጫቂ ሆኖ የከረመውና፣ የእንግሊዝ መንግስት ወደ አገሪቱ የሚገቡ ፍልሰተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የመወሰኑ ጉዳይ አግባብነት አለው ሲል በለንደን የሚገኝ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ ውሳኔ ሰጥቷል።

የሩዋንዳ መንግስትም ውሳኔውን እንደሚደግፍ ዛሬ ማስታወቁን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።

እንግሊዝ የአውሮፓ ኅብረትን ለቃ ከወጣች በኋላ ድንበሯን ጠንከር አድርጋ ለመቆጣጠር በመወሰኗ፣ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ፍልሰተኞች ጉዳይ አጨቃጫቂ ሆኖ ከርሟል።

በሕጉ መሠረት፣ ካለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ ወደ አገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ፍልሰተኞች ተይዘው ወደ ሩዋንዳ ይላካሉ።

ባለፈው ሰኔ ፍልሰተኞችን ይዘው ወደ ሩዋንዳ ሊያቀኑ የነበሩ አውሮፕላኖች፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ለፍርድ ቤት በማመልከታቸው፣ በረራቸው ተሰርዟል። ዛሬ ሰኞ ግን በለንደን የሚገኙ ዳኞች ፍልሰተኞች ወደ ሩዋንዳ መላካቸው ሕጋዊ ነው ብለዋል።

ፍልሰተኞቹን ለማስተናገድ ሩዋንድ ከእንግሊዝ 146 ሚሊዮን ዶላር ትቀበላላች።

XS
SM
MD
LG