በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትዊተር ተጠቃሚዎች ኢላን መስክ ከዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲነሱ ጠየቁ


ፋይል - የተስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢላን መስክ በጀርመን፣ በርሊን የሚገኘው የተስላ ማምረቻ ምርቃት ላይ March 22, 2022.
ፋይል - የተስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢላን መስክ በጀርመን፣ በርሊን የሚገኘው የተስላ ማምረቻ ምርቃት ላይ March 22, 2022.

በቅርቡ ትዊተርን ገዝተው ዋና ሥራ አስፍፈጻሚ የሆኑት ኢላን መስክ፣ ተጠቃሚዎች በእርሳችው ላይ ድምጽ እንዲሰጡ በጠየቁት መሠረት ከ17 ሚሊዮን 500 ሺህ በላይ ከሚሆኑ ተሳታፊዎች ውስጥ 57.5 በመቶ የሚሆኑት ከሥራ አስፈጻሚነታቸው እንዲነሱ ድምጽ ሰጥተዋል።


ኢላን መስክ ለውሳኔው እንደሚገዙ አስታውቀዋል።


ድምጽ አሰጣጡ ከተፈጸመ በኋላ ግን ከኢላን መስክም ሆነ ከትዊተር ዋና መስሪያ ቤት የተሰጠ መግለጫ የለም።


መስክ ከትዊተር ተጠቃሚዎች ጋር ሲጋጩ ሰንብተዋል። ተፎካካሪ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች በትዊተር እንዳይጠቀሱ ለማድረግ መሞከራቸው ስህተት እንደነበር አምነው ተጠቃሚዎች በእርሳቸው ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ በመቆየት ላይ ድምጽ እንዲሰጡ ትናንት እሁድ ጠይቀው ነበር።


የኢላን መስክ አውሮፕላን ያለበትን ቦታ ስለሚከታተለው ትዊትር ገጽ የጻፉ በርካታ ጋዜጠኞች ባለፈው ሳምንት ገጻቸው እንዲታገድ ተደርጓል። ኢላን መስክ በጉዳዩ ላይ ተጠቃሚዎች ድምጽ እንዲሰጡ ካደረጉ በኋላ፣ መልሶ እንዲከፈትላቸው የሚጠይቀው ድምጽ ብልጫ በማግኘቱ ታግደው የነበሩት የጋዜጠኞች ገጽ ተመልሰው ተከፍተዋል።


ገጻቸው ታግዶ ከነበሩት መሃል የቪ.ኦ.ኤ፣ ሲ.ኤኔ.ኤን፣ ኒው ዮርክ ታይምስ እና ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኞች ይገኙበታል።

XS
SM
MD
LG