በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩጋንዳ የኢቦላ መነሻ በነበሩት ወረዳዎች ላይ የጣለችውን ክልከላ አነሳች


ፋይል - በዩጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት፣ ካምፓላ የሚገኙ ሞተረኞች እና ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ መብራት ላይ ቆመው
ፋይል - በዩጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት፣ ካምፓላ የሚገኙ ሞተረኞች እና ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ መብራት ላይ ቆመው

ዩጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ ማዕከል በሆኑት ሁለት ወርዳዎች ላይ ለሁለት ወር ጥላው የነበረውን ከቤት ያለመውጣት ክልከላ፣ ወረርሽኙ በቅርቡ ሊያከትም ይችላል በሚል ተስፋ አንስታለች።


የዩንጋዳ ባለስልጣናት የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን ካወጁበት ከመስከረም 20 አንስቶ ሀገሪቱ 142 በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎችን እና 52 ሞቶችን የመዘገበች ሲሆን፣ በሽታው ወደ ዋና ከተማው ካምፓላ ተዛምቶ ነበር።

በመሆኑም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ፣ ወረርሽኙ በተነሳባቸው ሁለቱ ወረዳዎች ሙቤንዴ እና ካሳንዳ ከቤት ያለመውጣት ክልከላ እንዲታወጅ በመወሰናቸው የገበያ ቦታዎች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ቤተክርስቲያናት እና ማንኛውም ጉዞ ታግረደው ቆይተዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ዩጋንዳ የመጀመሪያውን ለሱዳኑ የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ የሚሆን የሙከራ ክትባት የተረከበች ስሆን ክትባቱ በቫይረሱ ለተያዙ ህሙማን፣ ከነሱ ጋር ንክኪ ለነበራቸውና ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው አንድ ወረርሽኝ ማብቃቱ የሚታወቀው ለ42 ተከታታይ ቀናት አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ህመምተኛ ሳይኖር ሲቀር ነው።

XS
SM
MD
LG