በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ተከበረ


ፋይል - በግሪክ ክሬት ደሴት በተደረገ ነፍስ አድን ዘመቻ፣ በፔሊኦክራ ወደብ ላይ ስደተኞች ለአሳ ማጥመጃ የሚሆን ጀልባ ላይ ተሳፍረው Nov. 22, 2022.
ፋይል - በግሪክ ክሬት ደሴት በተደረገ ነፍስ አድን ዘመቻ፣ በፔሊኦክራ ወደብ ላይ ስደተኞች ለአሳ ማጥመጃ የሚሆን ጀልባ ላይ ተሳፍረው Nov. 22, 2022.

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ እሁድ ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ቀን ያከበረ ሲሆን እለቱ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በርካታ ተግዳሮቶች ያጋጠሟቸው በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚታወስበት ነው ተብሏል።

የዚህ አመቱ የስደተኞች ቀን የሚከበረው ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ የአውሮፓ ሀገራት ከአፍጋኒስታን፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ለሚመጡ ስደተኞች እና የኢኮኖሚ ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ በራቸውን እየዘጉ በመጡበት ወቅት ሲሆን፣ ደቡባዊውን የዩናይትድ ስቴትስ ድንበር አልፈው ለመግባት የሚሞክሩ ከመካከለኛ አሜሪካ የሚነሱ ስደተኞች ቁጥርም እንዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ሰዎች ያለምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው አይሰደዱም ያለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ሰዓት ካሉት 280 ሚሊየን ዓለም አቀፍ ስደተኞች ውስጥ አብዛኞቹ በግጭት፣ በስቃይ፣ በከፋ ድህነት እና እየጨምረ በመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለስደት መዳረጋቸውን አስታውቋል።

ህጋዊ መንገድ መከተል ያልቻሉ በርካታ ስደተኞች ጥገኝነት ለመጠየቅ አድገኛ መንገዶችን የሚከተሉ ሲሆን አብዛኞቹ ለብዝበዛ፣ እንግልት እና በመንገድ ላይ ሳሉ ለሞት ተዳርገዋል። የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ባወጣው መረጃ፣ ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞች ሞተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ጠፍተዋል ብሏል።


የስደተኞች መብቶች ሰብዓዊ መብቶች ናቸው፣ በመሆኑም ያለአድሎ ሊከበሩ ይገባል ያለው የመንግስታቱ ድርጅት እነዚህ መብቶች ሰዎች በግዳጅ እንዲሰደዱ ተደርገውም ሆነ በፈቃደኝነት ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ግዜ ተፈፃሚ ይሆናሉ ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG