በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋይት ኃውስ በየመን ጦርነት ለሳዑዲ የሚሰጠው ድጋፍ እንዳይቆም ተከላከለ


ፋይል - የመኖች በሳዑዲ አረብያ የሚመራው የአየር ጥቃት በሰነዓ የሚገኙ ሁለት ቤቶች ላይ ያደረሰውን ጉዳት እየመረመሩ
ፋይል - የመኖች በሳዑዲ አረብያ የሚመራው የአየር ጥቃት በሰነዓ የሚገኙ ሁለት ቤቶች ላይ ያደረሰውን ጉዳት እየመረመሩ

ዋይት ኃውስ ዩናይትድ ስቴትስ ሳዑዲ አረብያ በየመን ለምታደርገው ጦርነት የሚሰጠውን ድጋፍ ሊያስቆም የነበረውን እና በህግ መወሰኛ ምክርቤት የቀረበውን የጦር ኃይሎች ውሳኔ ለማገድ መወሰኑን ደግፎ ተከላክሏል።


አርብ እለተ ከአሜሪካ ድምፅ ቃለመጠይቅ ያደረጉት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ "ሰላሙ ዘላቂ ሆኖ ማየት እንፈልጋለን። እናም ዲፕሎማሲያችን ስኬታማ መሆኑን ስለማረጋገጥ ስንናገር ያንን ማለታችን ነው" ብለዋል።


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሰረት በየመን የሚካሄደው ጦርነት 370 ሺህ ሰዎችን ህይወት ያጠፋ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው ያለፈው ጦርነቱ ባስከተለው የምግብ፣ ውሃ እና የጤና አገልግሎት እጥረት ነው።


በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የቨርሞንት ገለልተኛ የምክር ቤቱ አባል አሜሪካ ሳዑዲ በየመን ለምታካሂደው ጦርነት አሜሪካ የምታደርገው ድጋፍ የሚያቋርጥ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረባቸውን ተከትሎ የባይደን አስተዳደር ከበርኒ ሳንደርስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ ነበር። ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸውን እንደሚጠቀሙ ማሳወቃቸውን እና ከሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ድጋፍ ማጣቱን ተከትሎ ሳንደርስ የውሳኔ ሀሳባቸውን በማንሳት ከዋይት ኃውስ ጋር ለመደራደር ተስማምተዋል።

ሆኖም የአስተዳደሩ ኃላፊዎች በምን ጉዳይ ላይ ከሳንደርስ ጋር እንደሚደራደሩ ከመናገር ተቆጥቧል።

XS
SM
MD
LG