የአልሻባብ ታጣቂዎች የሚይዟቸውን ከተሞች እና መንደሮች የመንግሥት ኅይሎች ሊያስለቅቋቸው መሆኑን ሲያውቁ ህዝቡን ሆን ብለው ያፈናቅሉታል ሲል የሶማሊያ የጦር ኅይል ወነጀለ፡፡
አልሻባብ ሆን ብሎ ይህን የሚያደርገው ህዝቡ ከመንግሥት ጋር እንዳይተባበር ለማድረግ መሆኑን የጦር ኅይሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
አልሻባብ ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢው በራሳቸው ተነሳሽነት ተደራጅተው ከመንግሥት ጎን ሆነው የሚዋጉ ሰዎችን ለመበቀል ቤተሰቦቻቸውን ይጠልፋል ብለዋል፡፡ ወታደሮቹ የአልሻባብ ታጣቂዎችን ቢያንስ ሰባ ከሚሆኑ ቦታዎች እንዳስወጡ የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል፡፡