በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩኤስ- አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ሁለተኛ ቀን ውሎ


የዩኤስ -አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:43 0:00

የዩኤስ -አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅኝት

በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካ መሪዎች የሁለተኛ ቀን ጉባዔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ከዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ወኪል አምባሳደር ካትሪን ታይ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍትህ መስሪያቤት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ከሆኑት ቤት ሻክ ጋር ተነጋግረዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለ49ኙ የአፍሪካ ሀገራት እና የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ባደረጉት ንግግር ከአዲሱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት ጋር ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን አስታውቀዋል። ዲሞክራሲን ለማጠናከርም አሜሪካ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት መስራቷን እንደምትቀጥልም አመልክተዋል።

የአፍሪካ እና የዩናይትድ ስቴትስን የመጪ ዘመን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብርን የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል፣ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ወደ 50 ለሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች ንግግር አድርገዋል።

/ሀብታሙ ስዩም እና ስመኝሽ የቆየ የጉባዔውን ውሎ ያስቃኙናል።/

XS
SM
MD
LG