በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የኮቪድ ክትባት ዘመቻ ጀምራለች


በቻይና የትኩሳት ወረሽኝ ሰልፍ
በቻይና የትኩሳት ወረሽኝ ሰልፍ

ቻይና የኮቪድ 19 ወረርሺኙ በፍጥነት እያሻቀበ መሆኑ ባመጣው ስጋት ለቫይረሱ በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎቿን ለመከተብ በመሯሯጥ ላይ ነች፡፡

ቻይና ላለፉት ሦስት ዐመታት ወረርሺኙን ገትቶት የነበረውን ዜሮ ኮቪድ ፖሊሲ ማርገቧን ተከትሎ በበሽታው የሚሞተው ሰው ቁጥር እንደሚያሻቅብ ተንታኞች ተንብየዋል፡፡

የዐለም የጤና ድርጅትም የኮቪድ መከላከያ ክትባት ለ1 ነጥብ 4 ቢሊዮኑ የቻይና ህዝብ በበቂ ሁኔታ እንዳልተዳረሰ በመግለጽ ስጋቱን አሰምቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ቻይናን እየተባባሰ ያለውን ወረርሽኝ እንድትቆጣጠር ለመርዳት ዝግጁነቷን ገልጻለች፡፡

ቤጂንግ ብዙ ዜጎቿን ጭንቀት ውስጥ የከተተውን እና ኢኮኖሚዋን የጎዳውን ዜሮ ኮቪድ የተባለውን ጥብቅ ፖሊሲ ባለፈው ረቡዕ መሰረዝ ጀምራለች፡፡

XS
SM
MD
LG