በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ የዋንጫ ጉዞ እና ምባፔ


ቲዮ ኸርናንዴዝ በሞሮኮ ላይ ግብ ሲያስቆጥር
ቲዮ ኸርናንዴዝ በሞሮኮ ላይ ግብ ሲያስቆጥር

በትላንትናው ዕለት እ.ኤ.አ በታህሳስ 14 ቀን 2022 ዓ.ም የፈረንሳይ ቡድን ሞሮኮ አቻውን 2-0 በሆነ ውጤት ካሸነፈ በኋላ የፈረንሳዩ ኪሊያን ምባፔ የሞሮኮውን አቻራፍ ሃኪሚን ሲያቅፍ ታይቷል።

ሞሮኮ በፊታችን ቅዳሜ ለሦስተኛ ደረጃ የፍጻሜ ጨዋታ ክሮኤሺያን ትገጥማለች።

እረቡ ዕለት በአል ኮኸር ካታር በተካሄደው ጨዋታ ፈረንሳዊው ቴዎ ሄርናንዴዝ በአምስተኛው ደቂቃ፤ እንዲሁም ራንዳል ኮሎ ሙአኒ በ79ኛው ደቂቃ ጎል ያስቆተሩ ሲሆን፤ ፈረንሳይ ሞሮኮን 2-0 በማሸነፍ የካታር የአለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ተጠናቋል።

በመጪው እሁድም የአለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይ ከአርጀንቲና ጋር ትገጥማለች።

ፈረንሳዮች የሞሮኮውን አስደናቂ የሆነ ሩጫ ተቋቁመው ጨርሰዋል። ሞሮኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ረዥም ርቀት የተጓዘች አፍሪካዊት ሀገር በመሆን ድል አስመዝግባለች።

XS
SM
MD
LG