በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ኪቭ ላይ በኢራን ድሮኖች ጥቃት አደረሰች


የዩክሬን የፖሊስ ሃላፊ
የዩክሬን የፖሊስ ሃላፊ

ሩሲያ በኢራን በተሰሩ ድሮኖች ኪቭ ከተማ ላይ ባካሄደችው ጥቃት የመንግሥት ህንጻዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዩክሬን ባለስልጣናት ገለጹ

የመዲናዋ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ በሰጡት መግለጫ በማዕከላዊ ኪቭ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን ገልጸዋል። በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ለጊዜው በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

የዩክሬን የጦር ኃይል 13 ኢራን ሰር ሻሂድ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ ፅህፈት ቤት ሹም እንዳስታወቁት ዩክሬን እና ሩስያ የእስረኛ ልውውጥ አካሂደዋል። በእስረኛ ልውውጡ ምስራቅ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ውስጥ ሲዋጉ የተማረኩ 64 የዩክሬን ወታደሮች መለቀቃቸው ታውቋል። በእስረኛ ልውውጡ ከተለቀቁት መካከል አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋም እንደሚገኝበት ባለስልጣኑ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG