No media source currently available
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ለሁለት ዓመት የመብራት አገልግሎት ተቋርጦባት የነበረችው የሁመራ ከተማ ከትናንት ጀምሮ አገልግሎቱን ዳግም ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ባለፉት ሦስት ቀናት ሁመራንና ማይጨውን ጨምሮ ከአምስት ከተሞች በላይ የመብራት አገልግሎት መጀመሩንና አክሱም፣ አድዋ፣ አዲግራትና ውቅሮን ተጠቃሚ ለማድረግም እንደሚሠራ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይ ያዳምጡ/ መስፍን አራጌ