የኢራን መንግሥት በሀገሪቱ እስልምና ካልሆኑ ዕምነቶች ውስጥ ትልቁ በሆነው የባሃይ እምነት ላይ በቀጠለው አፈና ሁለቱን መሪዎች ማሰሩን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማህበረሰቡ ተወካዮች ትናንት ዕሁድ አስታውቀዋል።
የስድሳ ዘጠኝ ዐመቷ ማህቫዥ ሳቤት እና የስድሳ አመቷ ፋሪባ ካማላባዲ ካህን ቀደም በባሃዮች ትግል አንቂነታቸው የተነሳ ሁለቱም ለአስር ዐመታት ታስረው የነበሩ ሲሆን በቅርቡ አንድ ሰዐት በፈጀ የፍርድ ሂደት አዲስ የአስር አመት እስራት እንደተፈረደባቸው ገልጸዋል። ሁለቱ ሴቶች የታሰሩት ባለፈው ሃምሌ ወር መሆኑን የባሃዮች አለም አቀፍ ማህበረሰብ አስታውቋል።