በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በየመን በጦርነቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት 11 ሺህ ህጻናት ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል" ተመድ


ፋይል - አንዲት ህፃን በሳናአ፣ የመን ዳርቻ ላይ በሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በሚገኘው የቤተሰቦቿ ጎጆ ውጪ ቆማ ትታያለች።
ፋይል - አንዲት ህፃን በሳናአ፣ የመን ዳርቻ ላይ በሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በሚገኘው የቤተሰቦቿ ጎጆ ውጪ ቆማ ትታያለች።

በየመኑ ጦርነት እ.አ.አ ከ2015 ዓመተ ምህረት ወዲህ ከ11 ሺህ የሚበልጡ ህጻናት ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተናገረ።

አሃዙ ሳውዲ መሩ ህብረት ግጭቱን በተቀላቀለበት ጊዜ በድርጅቱ የተረጋገጡ ክስተቶችን ብቻ ያካተተ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።

የዩኒሴፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ካትሪን ረስል ባወጡት መግለጫ" ብዙ ሺህ ህጻናት ህይወታቸውን አጥተዋል። አሁንም ብዙ መቶ ሺህ ህጻናት ለመከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ወይም በረሃብ ሳቢያ ሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ " ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳመለከተው ከየመን ህዝብ ሶስት አራተኛ የሚሆነው ሰብዐዊ ዕርዳታ እና የደህንነት ጥበቃ ያስፈልገዋል።

XS
SM
MD
LG