በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ከተቃውሞ ሰልፉ በተያያዘ ሁለተኛ የሞት ቅጣት ፈጸመች

በቆጵሮስ ዋና ከተማ ኒኮሲያ ውስጥ አንድ ሰው እ.አ.አ በታህሳስ 12፣ 2022 ዓ.ም የኢራን ባለስልጣናት ለሶስት ወራት ከሚጠጋ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመዋን የማጂድሬዛ ራህናቫርድን የሞት ቅጣት አስመልክቶ የትዊተር ያሰፈሩትን መልዕክት በስልኩ ላይ ሲመለከት
በቆጵሮስ ዋና ከተማ ኒኮሲያ ውስጥ አንድ ሰው እ.አ.አ በታህሳስ 12፣ 2022 ዓ.ም የኢራን ባለስልጣናት ለሶስት ወራት ከሚጠጋ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመዋን የማጂድሬዛ ራህናቫርድን የሞት ቅጣት አስመልክቶ የትዊተር ያሰፈሩትን መልዕክት በስልኩ ላይ ሲመለከት

ኢራን ባለፈው መስከረም ከተቀሰቀሰው የተቃውም ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ በሚገኝ ሁለተኛ ሰው ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሟን አስታወቀች።

ማጂድሬዛ ራናቫርድ ዛሬ ማሻድ ከተማ ውስጥ በአደባባይ ተሰቅሏል ሲል ሚዛን የተባለው የኢራን መንግሥት የፍትህ ዘርፍ የዜና ወኪል አስታውቋል።

ራህናቫድ ባለፈው ወር በከተማዋ ሁለት የጸጥታ ኃይል አባላትን በስለት ገድሏል ተብሎ ተፈርዶበት እንደነበር ታውቋል።

የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሪዎች እንዳሉት በኢራን ቢያንስ 12 ሰዎች በዝግ ችሎት የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ሲሆን ከተቃውሞው በተያያዘ የመጀመሪያው የሞት ቅጣት ባለፈው ሳምንት መፈጸሙ ይታወሳል።

የኢራናውያኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ የጀመረው ሂጃብ በትክክል አልተከናነብሽም ተብላ በሀገሪቱ የስነ ስርዐት ፖሊስ የተያዘቸው የ22 ዐመት ወጣት ማህሳ አሚኒ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆና ህይወቷ ካለፈ በኋላ መሆኑ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG