በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ጦርነት ላይ የተገደለው ዛምቢያዊ አስከሬን ወደ ሀገሩ ተወስዷል


የዛምቢያዊውን ተማሪ ሌሜካኒ ኒሬንዳ አስክሬን የጫነ መኪና በሉሳካ፣ ዛምቢያ እ.አ.አ ታህሳስ 11 2022 ዓ.ም ኬኔት ካውንዳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ቤተሰቦቹ ተቀብለውታል።
የዛምቢያዊውን ተማሪ ሌሜካኒ ኒሬንዳ አስክሬን የጫነ መኪና በሉሳካ፣ ዛምቢያ እ.አ.አ ታህሳስ 11 2022 ዓ.ም ኬኔት ካውንዳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ቤተሰቦቹ ተቀብለውታል።

በሩስያ የጦር ሰራዊት ውስጥ ተሰልፎ በዩክሬን ጦርነት ሲዋጋ የተገደለው የ 23 ዐመቱ ዛምቢያዊ ተማሪ አስከሬን ወደሀገሩ ተወስዷል።

የሩስያ የጦር ሰራዊትን ከመቀላቀሉ አስቀድሞ ሩስያ ውስጥ የኒውክሊየር ምህንድስና ትምህርት በማጥናት ላይ የነበረው ዛምቢያዊ ተማሪ ሌሜካኒ ኒሬንዳ አስክሬን ትናንት ዕሁድ ሉሳካ ገብቷል።

ዛምቢያዊው በነጻ ትምህርት ዕድል ትምህርቱን እየተከታተለ የነበረ ቢሆንም እ.አ.አ በ2020 ዐመተ ምህረት ሚያዚያ ወር ላይ ሱስ አስያዥ መድሃኒቶችን በማስተላለፍ ወንጀል የዘጠኝ ዐመት እስራት ቅጣት ተፈርዶበት እንደነበር ዘገባው አመልክቷል። በኋላም በውጊያው በመካፈል የተሰጠውን ልዩ ምህረት ተቀብሎ ዩክሬን ውስጥ ውጊያ ላይ ተገድሏል።

የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቲር ስታንሊ ካኩቦ መንግሥታቸው ስለዛምቢያዊው አሟሟት ከሩሲያ ባለስልጣናት ማብራሪያ መጠየቁን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ባወጡት መግለጫ "ተማሪው እ.አ.አ ነሃሴ 23 በቅድመ ሁኔታ ምህረት ተደርጎለት በልዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲካፈል ተፈቅዶለት ከገባ በኋላ መስከረም ወር ውስጥ ተገድሏል" የሚል ማብራሪያ ተሰጥቶናል ብለዋል።

የሟቹን ማንነት የሚያረጋግጥ የአስክሬን ምርመራ መደረጉን እና የሩሲያ መንግሥት ለቤተሰቦቹ ካሳ እንደሚከፍል ሚንስትሩ አክለው አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG