በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞሮኮ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈች፤ትኬት ጠፍቷል


የዛሬው ቅዳሜ የሞሮኮ እና ፖርቱጋል ጨዋታ ዲሴምበር 10 2022
የዛሬው ቅዳሜ የሞሮኮ እና ፖርቱጋል ጨዋታ ዲሴምበር 10 2022

ካታር በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ የፖርቹጋልን ቡድንን 1 ለ ዜሮ ያሸነፈችው ሞሮኮ ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ማለፏን ያረጋገጠች የመጀመሪያዋ አፍሪካ ሀገር ሆናለች፡፡

ያልተጠበቀ ፉክክርና ውጤቶች በታዩበት በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሞሮኮ ዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 1/2015 ዓ.ም ሞሮኮ ለአፍሪካና ለአረቡ ዓለም ታሪክ ሠርታለች፡፡

ዩሱፍ ኤን ኔሲሪ ከእረፍት በፊት በነበረው ጨዋታ፣ በአየር ላይ ያገኛትን ኳስ በጭንቅላቱ ደፍቆ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሞሮኮ ወደ ሚቀጥሉት ጥቂት ቡድኖች መሸጋገር ችላለች፡፡

የሞሮኮ ተጫዋቾች ከድል በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ
የሞሮኮ ተጫዋቾች ከድል በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ

ቤልጅየምና ስፔይንን ድል እየነሳች የመጣችው ሞሮኮ ዛሬ ደግሞ ፖርቱጋልን በመርታት በሚቀጥለው ረቡዕ ከፈረንሳይና እንግሊዝ አሸናፊ ጋር ትገጥማለች፡፡ዛሬ በተገኘው አስደናቂ ድል በአፍሪካና አረቡ ዓለም ፌሽታ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በሌላም በኩል ላይ በስቴዲዮም ተገኝቶ ለመመልከት ትኬት ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ተነግሯል።ካታር እስካሁን የዛሬ አራት ኣመት 2011 ላይ ሞስኮ ላይ ከተሸጠው ትኬት በላይ መሸጧን የመንግሥት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

1.33 ሚሊዮን ለሚሆኑ ተመልካቾች 3.09 ሚሊዮን ትኬቶች መሸጣቸውን ነው ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።ይሁን እንጂ ፊፋ ስለ ተባለው ቁጥር አስተያየት አልሰጠም።ይሁን እንጂ ፊፋ ስለ ተባለው ቁጥር አስተያየት አልሰጠም።

በአረቡ ዓለም የመጀመሪያው የሆነውን የዓለም ዋንጫ ለመመልከት የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች፣ በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ የአካባቢው የአረብ አገሮች፣ ከ64ቱ ጨዋታዎች የቀሩትን 6 ጨዋታዎች ብቻ ለመመልከት ከፍተኛ ፍለጋ ላይ እንደነበሩ ዘግቧል።

አንዳንዶቹም የትኬት ሽያጭ አለ የሚል ወሬ በመስማታቸው በስቴዲዮም መግቢያዎች የተሰለፉ መሆናቸውም ተነግሯል።

የፊፋ ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ግን ትኬት ፍለጋ ለተሰለፉት ምንም የሚሸጥ ነገር አለመኖሩን እያስታወቁ መሆኑ ተዘግቧል።

ዛሬ ቅዳሜ በሞሮኮ እና ፖርቱጋል እንዲሁም እንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል የሚካሄዱትን ጨዋታዎች ለማየት በርካታ ተመልካቾች ከፍተኛ ጉጉትና ጭንቀት ማሳየታቸው ተዘግቧል።

"ወደ እዚህ ቦታ ብዙ ተመላልሻለሁ ወደ ስቴዲዮሙ ገብቼ ለመመልከት የቻልኩት ግን ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ነው። ይኸው ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኖኛል ምንም ትኬት የለም” ሲሉ ካታር ሆቴል ውስጥ የሚሰሩ አንድ የባንግላዴሽ ዜጋ ተናግረዋል።

የዶሃ ጨዋታ ከጀመረ አንስቶ በካታር የሚገኝ መሆኑን የገለጸው የአርጀንቲናው ደጋፊ ኒኮላስ ሄርማኖስ ትኬት ለማግኘት እየተቸገረ መሆኑን ገልጾ "አርጀንቲና እየቆየ በሄደ ቁጥር ትኬት ማግኘቱ አዳጋች መሆኑን" ተናግሯል።

"የሜሲን የመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ጫዋታ መመልከት የግድ ነው" ያሉት ተመልካቾችም መኖራቸው ተነገሯል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሸጡ ትኬቶች መኖራቸው ቢነገርም እርግጠኝነታቸው አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG