በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ጉባኤ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ዋሽንተን ዲሲ 2015 ዓ.ም/2022 1024x647.gif
የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ዋሽንተን ዲሲ 2015 ዓ.ም/2022 1024x647.gif

በፕሬዚዳንት ባይደን አዘጋጅነት ወደ 50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ እና የዳያስፖራው ማህበረሰብ ተካፋይ እንደሚሆኑ የሚጠበቅበት፣ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የፊታችን ማክሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄድ ሲሆን ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተመለከተ።

የአፍሪካ ዲፕሎማቶች ቡድን መሪ የኮንጎ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሰርጌ ሞምቡሊ፣ ከዋይት ሀውስና ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለወራት ዝግጅት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ጉባኤው በዩናይትድ ስቴትስና በተናጠል ከአፍሪካ አገሮች ጋር እንዲሁም የሁለዮትዮሽና በአፍሪካ ደረጃ ያለውን ግንኙነትና ትብብር ያጠናክራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ አምባሰደሩ ተናግረዋል።

ይህ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ የወደፊቱን የአፍሪካ ሁለንተናዊ የአፍሪካ ህብረት ፍኖተ ካርታ የሆነውን አጀንዳ 2063 ለመደገፍ ያስችላታል ብለው እንደሚጠበቁም አምባሰደሩ ተስፋ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

የመጀመሪያውን የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ጉባኤ እኤአ በ2014 ያስተናገዱት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ መሆናቸው ይታወቃል።

ጉባኤው እየተባባሰ በመጣው የአፍሪካ ንብረት ላይም እንደሚነጋገር ተነገሯል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ የሙቀት መጠን ከሌሎች የዓለም ክፍሎች በበለጠ ሁኔታ በፍጥነት እየጨመረ መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ አፍሪካ ለዓለም አረንጓዴው ጋዝ ልቀት የምታበረክተው 4 ከመቶውን እጅ ብቻ መሆኑ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የ49 ሀገሮች መሪዎች የተጋበዙ ሲሆን ኤርትራ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው፣ እንዲሁም ሱዳንና ሌሎችም ሥልጣን በመፈንቅለ መንግሥት የያዙ መሪዎች ያሉባቸው ጥቂት ሃገሮች ከግብዣው ውጭ የተደረጉ መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG