በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ ክልል ይፈፀማሉ የተባሉ ጥቃቶችን የሚቃወሙ ሰልፎች ተካሄዱ


በኦሮሚያ ክልል ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች የሚያሳይ የጎግል ካርታ
በኦሮሚያ ክልል ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች የሚያሳይ የጎግል ካርታ

በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙና አንገር ጉቴ ወረዳዎች ውስጥ እየተፈፀሙ ነው በተባሉ ጥቃቶች ቁጥሩ የበዛ ሰው መገደሉና በሺሆች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው በተዘገበበት በዚህ ሳምንት በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል።

በኦሮምያ ክልል የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጆችና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በወለጋ ዞኖች ውስጥ ‘ታጥቀዋል’ ባሏቸው ቡድኖች ‘በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ይፈፀማሉ’ ያሏቸው ግድያዎችና ማፈናቀል እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያና እገታ መንግሥት እንዲያስቆም ለመጠየቅ ደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ሰልፍ መጠራቱንና ሱቆችን የመዝጋት አድማ ትናንት እና ዛሬ መካሄዱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በደቡብ ክልል ዲላ ውስጥም የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ መልዕክቶችን ይዘው ለየብቻቸው የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኦሮሚያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች መንግሥት አፋጣኝ መፍትኄ እንዲሰጥ አሳስቧል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:52 0:00

/በዚህ ዘገባ ላይ ናኮር መልካ፣ አስቴር ምስጋናውና ዮናታን ዘብዲዮስ አስተዋጾ አድርገዋል/

XS
SM
MD
LG