በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያው ፕሬዝዳንት ለስራ ጉብኝት አስመራ ገቡ


የኬንያው ፕሬዝዳንት አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስደርሱ
የኬንያው ፕሬዝዳንት አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስደርሱ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፡ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ህዳር 30፣ 2015 ዓ.ም አመሽሽ ላይ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ መሪዎች ከአየር ማረፊያ በቀጥታ ወደ ቤተ-መንግስት በማምራት በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ጉብኝት በሁለቱ ሀገራቱ መካከል የለውን ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ዛሬ ምሽት ለፕሬዝዳንት ዊሊያም በቤተ መንግስት የባህላዊ ሙዚቃና የራት ግብዣ እየተደረገላቸው ነው።

XS
SM
MD
LG